የኤል ኒኞ የአየር ንብረት ክስተት የሸንኮራ አገዳ ምርትን በመፈታተን የዓለምን የስኳር ዋጋ ሊያናረው እንደሚችል ተገለጸ - ባለሙያ
16:34 27.06.2026 (የተሻሻለ: 16:44 27.06.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የኤል ኒኞ የአየር ንብረት ክስተት የሸንኮራ አገዳ ምርትን በመፈታተን የዓለምን የስኳር ዋጋ ሊያናረው እንደሚችል ተገለጸ - ባለሙያ
የሩሲያ የግብርና ቢዝነስ እና የምግብ ዋስትና ማዕከል ኃላፊ አናቶሊ ቲኮኖቭ ለስፑትኒክ እንደተናገሩት፤ ለብዙ አስመጪ ሀገራት በተለይም በአፍሪካ እና በደቡብ እስያ የስኳር ዋጋ መናር መሠረታዊ የምግብ ፍጆታ ወጪን ከ10 እስከ 15 በመቶ ሊጨምረው ይችላል።
ኤል ኒኞ ጠንከር ያለ ጉዳት የሚያደርስ ከሆነ፤ ከዳካ እስከ ሌጎስ ያሉ የሱቅ መደርደሪያዎችም ጭምር ቀውሱ እንደሚያርፍባቸው አክለዋል።
በኤል ኒኞ ስጋት ምክንያት በለንደን የወደፊት የስኳር ግብይት ዋጋ እስከ ሰኔ መጀመሪያ ድረስ በአንድ ቶን ከ660 ዶላር በላይ ማለፉ የተዘገበ ሲሆን፤ ሕንድ እስከ መስከረም 20 ድረስ የስኳር ወጪ ንግዷን ማገዷን አስታውቃለች።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X