“አዋጁ በኢትዮጵያ ያለውን የምግብ ሥርዓት እና ሥርዓተ ምግብ ፈጣን ሽግግር ማምጣት ያስችለናል” – ኢትዮጵያዊ ባለሙያ

© telegram sputnik_ethiopia“አዋጁ በኢትዮጵያ ያለውን የምግብ ሥርዓት እና ሥርዓተ ምግብ ፈጣን ሽግግር ማምጣት ያስችለናል” – ኢትዮጵያዊ ባለሙያ
“አዋጁ በኢትዮጵያ ያለውን የምግብ ሥርዓት እና ሥርዓተ ምግብ ፈጣን ሽግግር ማምጣት ያስችለናል” – ኢትዮጵያዊ ባለሙያ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 27.06.2026
ሰብስክራይብ

“አዋጁ በኢትዮጵያ ያለውን የምግብ ሥርዓት እና ሥርዓተ ምግብ  ፈጣን ሽግግር ማምጣት ያስችለናል” – ኢትዮጵያዊ ባለሙያ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያፀደቀውን “ከእርሻ እስከ ጉርሻ” የምግብ ሥርዓት እና ሥርዓተ ምግብ አዋጅ አስመልክቶ፤ ታዋቂው የሳይንስ አማካሪ እና የሸማቾች መብት ተሟጋች ተባባሪ ፕሮፌሰር ዶ/ር አሻግሬ ዘውዱ ከአዋጁ አስፈላጊነትና ከሀገሪቱ ወቅታዊ የምግብ ዋስትና ቀውስ አንጻር ምልክታቸውን ለስፑትኒክ አፍሪካ አጋርተዋል።

 

“... የምግብ ሥርዓት እና የሥርዓተ-ምግብ ሥራ በፓርላማ የሚመራ፣ በጀት የሚመደብለት፣ የሚከታተል እና የሚደገፍ ይሆናል፤ ስለዚህ አሁን በኢትዮጵያ ያለውን የምግብ ሥርዓት እና ሥርዓተ-ምግብ ፈጣን ሽግግር ማምጣት ያስችለናል።”

 

በትምህርት ቤት ምገባ መርሃ-ግብር ብቻ የመቀንጨር ችግርን መፍታት እንደማይቻል የገለፁት ባለሙያው፤ አዋጁ ችግሩን ከምንጩ ለማድረቅ እንደሚረዳ አብራርተዋል””

 

“የአንድ ሕፃን አእምሮና ምርታማነት ገና በ2 ዓመቱ ነው የሚጎዳው። አእምሮው ሳይበለጽግ ትምህርት ቤት ቢመጣም ትምህርቱን ሊረዳ አይችልም። በአሁኑ ወቅት በሀገሪቱ ያለው የ40% የመቀንጨር መጠን ሙሉ በሙሉ 'የሕዝብ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ' ነው። በአንድ አገር ትክክለኛ የኢኮኖሚ ዕድገት እንዲመዘገብ የመቀንጨር መጠን ከአንድ አሃዝ (ከ10% በታች) ማነስ አለበት።”

 

በከተሞች የተሳሳተ የምግብ አጠቃቀምና የአኗኗር ዘይቤ ሳቢያ ከመጠን ያለፈ ውፍረት፣ ስኳር፣ ኮሌስትሮል እና ደም ግፊት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ እንደመገኘቱ የአዋጁ አስፈላጊነት የላቀ መሆኑን አስረድተዋል።

ዶ/ር አሻግሬ አክለውም፣ አዲሱ አዋጅ ለምግብ ደኅንነት ከፍተኛ ትኩረት መስጠት አለበት ብለዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ |

አዳዲስ ዜናዎች
0