በአበባ አበባ አቅመ ደካማ ዜጎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የ300 ሺህ ዶላር የኪዮስክ ግንባታ ፕሮጀክት በይፋ ተጀመረ
14:50 27.06.2026 (የተሻሻለ: 14:54 27.06.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
በአበባ አበባ አቅመ ደካማ ዜጎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የ300 ሺህ ዶላር የኪዮስክ ግንባታ ፕሮጀክት በይፋ ተጀመረ
የተባበሩት መንግሥታት የሰፈራ ፕሮግራም ፣ የአዲስ አበባ ከተማ የሥራና ክህሎት ቢሮ እንዲሁም የሥራ ቦታዎች ልማትና አስተዳደር ኤጀንሲ ከሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር “አዲስ ተስፋ” የተሰኘውን የመጀመሪያ ምዕራፍ የኪዮስክ ፕሮጀክት በይፋ አስጀምረዋል።
ፕሮጀክቱ በዋና ከተማዋ ለሚገኙ አቅመ ደካማ፣ ሥራ አጥ እና ከተለያዩ ሀገራት ለተመለሱ ዜጎች ቋሚ የሥራና የገቢ ዕድል ለመፍጠር ያለመ ነው።
ለፕሮጀክቱ አጠቃላይ 300 ሺህ የአሜሪካ ዶላር በጋራ ፈሰስ እንደሚደረግ የተገለፀ ሲሆን በአዲስ አበባ በተለያዩ አካባቢዎች 100 ዘመናዊ የንግድ ኪዮስኮች ይገነባሉ ተብሏል።
የፕሮጀክቱ የግንባታ ሂደት ሲጠናቀቅ ከ200 በላይ ለሚሆኑ አቅመ ደካማ ዜጎች አስተማማኝና ዘላቂ የገቢ ምንጭ ይፈጥራል ተብሎ ይጠበቃል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X