የሀገራዊ የከተማ የመጠጥ ውሃ ሽፋን 84.31 በመቶ ደርሷል – የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር

ሰብስክራይብ

የሀገራዊ የከተማ የመጠጥ ውሃ ሽፋን 84.31 በመቶ ደርሷል – የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር

ሚኒስትር ዴኤታ ተስፋዬ ፊቻላ፣ የገጠር መጠጥ ውሃ ሽፋን 69.03 በመቶ መድረሱንም የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በአዲስ አበባ ቦሌ ለሚ ልዩ ኢኮኖሚክ ዞን ባካሄዱት 11ኛው ሀገር አቀፍ የወር አበባ ጤና እና ንፅህና አጠባበቅ ጉባኤ ላይ ገልፀዋል፡፡

ቀጣይ ሀገራዊ የመጠጥ ውሃ ሽፋንን 76.67 በመቶ በማድረስና የንፁህ ውሃ አቅርቦት ችግርን በመፍታት፣ ኢትዮጵያን ለወር አበባ ንፅህና አጠባበቅ ተስማሚ ለማድረግ ሚኒስቴሩ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት ይሰራል ብለዋል።

የትምህርት ሚኒስቴር፣ ዩኒሴፍ ፣ ዩኤንኤፍፒኤ እና ሲሲአርዲኤ ተወካዮች የወር አበባ ጉዳይ የጤና፣ የትምህርትና የመብት ጉዳይ መሆኑን በመጥቀስ ችግሩን በጋራ ለመፍታት የሚያስችል ስምምነት ተፈራርመዋል።

ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የማኅበራዊ ሚዲያ ገጽ የተገኘ ቪዲዮ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0