በአምቦ፣ ነቀምት እና አሶሳ ከተሞች የኃይል መቆራረጥን የሚቀንስ የ3 ቢሊዮን ብር ስምምነት ተፈረመ

© telegram sputnik_ethiopiaበአምቦ፣ ነቀምት እና አሶሳ ከተሞች የኃይል መቆራረጥን የሚቀንስ የ3 ቢሊዮን ብር ስምምነት ተፈረመ
በአምቦ፣ ነቀምት እና አሶሳ ከተሞች የኃይል መቆራረጥን የሚቀንስ የ3 ቢሊዮን ብር ስምምነት ተፈረመ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 27.06.2026
ሰብስክራይብ

በአምቦ፣ ነቀምት እና አሶሳ ከተሞች የኃይል መቆራረጥን የሚቀንስ የ3 ቢሊዮን ብር ስምምነት ተፈረመ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በአምቦ፣ ነቀምት እና አሶሳ ከተሞች የሚገኙ የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማቶችን ለማዘመን ከአልፋ ቲኤንዲ እና ካፒታል ከተሰኙ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች ጋር የ3 ቢሊዮን ብር ስምምነት ተፈራርሟል።

በ2 ዓመታት ውስጥ ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ለአገልግሎት ይበቃል የተባለው በፕሮጀክቱ፦

325 ኪሎ ሜትር የመካከለኛ ቮልቴጅ መስመር ዝርጋታና ማሻሻያ ይደረጋል።

በአጠቃላይ 235 ትራንስፎርመሮች የሚታደሱ ሲሆን (70 በአምቦ፣ 121 በነቀምት፣ 44 በአሶሳ) ይከናወናል።

የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጌቱ ገረመው፣ ፕሮጀክቱ በከተሞቹ ያለውን የኃይል መቆራረጥና የቴክኒክ ችግር በዘላቂነት ስለሚቀንስ፥ ተቋራጮች በተያዘለት ጊዜና ጥራት እንዲያጠናቅቁ አሳስበዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0