የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አዲስ የትራፊክ አደጋ መረጃ አስተዳደር ሥርዓት ወደ ሥራ አስገባ

© telegram sputnik_ethiopiaየኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አዲስ የትራፊክ አደጋ መረጃ አስተዳደር ሥርዓት ወደ ሥራ አስገባ
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አዲስ የትራፊክ አደጋ መረጃ አስተዳደር ሥርዓት ወደ ሥራ አስገባ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 27.06.2026
ሰብስክራይብ

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አዲስ የትራፊክ አደጋ መረጃ አስተዳደር ሥርዓት ወደ ሥራ አስገባ

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት ጋር በጋራ ሲያበለፅጉት የቆዩትን ይህ ሥርዓት፤ ከዚህ ቀደም በወረቀት ይላኩ የነበሩ፣ ታማኝነት የጎደላቸውና ወጥ ያልሆኑ ሪፖርቶችን ሙሉ በሙሉ እንደሚያስቀር ተገልጿል፡፡

"ከአሁን በኋላ ትክክለኛ የትራፊክ መረጃዎችን ሌላ ሰው ሊነግረን አይገባም" ያሉት የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል ርስቱ ይርዳው በትግበራ ወቅት ወደ ኋላ የሚቀር ክልል ወይም አካባቢ ሊኖር እንደማይገባ አሳስበዋል፡፡

የመረጃ ሥርዓቱ ዋና ዋና አገልግሎቶችና ፋይዳዎች፦

🟠ለመላው የሀገሪቱ የፖሊስ ሠራዊት አባላትና ለትራፊክ ደህንነት ባለሙያዎች ፈጣንና አስተማማኝ መረጃ ተደራሽ ያደርጋል።

🟠የትራፊክ አደጋ ተጎጂዎች፣ ባለንብረቶች፣ ኢንሹራንስ ሰጪዎች እና ፖሊሲ አውጪዎች የሚፈልጉትን መረጃ በአንድ ማዕከል እንዲያገኙ ያስችላል።

🟠የመንግሥት አካላት በተደራጀና በተተነተነ መረጃ ላይ በመመሥረት የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ ስልታዊ እርምጃዎችን እንዲወስዱ ያግዛል።

🟠በሀገሪቱ የመንገድ ደህንነት ላይ የሚታዩ ችግሮችን በመረጃ (ዳታ) ላይ ተመስርቶ ለመገምገምና ለመፍታት ያስችላል።

ፌደራል ፖሊስ የትራፊክ አደጋ መረጃ አስተዳደር ሥርዓቱን ከመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት በትናንትናው ዕለት በይፋ ተረክቧል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0