“ከእርሻ እስከ ጉርሻ”፦ የምግብ ዋስትናን በዘላቂነት ለማረጋገጥ ያስችላል የተባለው የምግብ ሥርዓት እና ሥርዓተ ምግብ ረቂቅ አዋጅ ጸደቀ
10:29 27.06.2026 (የተሻሻለ: 10:34 27.06.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
“ከእርሻ እስከ ጉርሻ”፦ የምግብ ዋስትናን በዘላቂነት ለማረጋገጥ ያስችላል የተባለው የምግብ ሥርዓት እና ሥርዓተ ምግብ ረቂቅ አዋጅ ጸደቀ
በረቂቅ አዋጁ ላይ በስፋት የተወያየው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፤ የአዋጁ መጽደቅ የሀገሪቱን ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ለማፋጠን እንዲሁም የምግብ ደህንነትን አስተማማኝ ለማድረግ ትልቅ ምዕራፍ እንደሚሆን በመገንዘብ በሙሉ ድምፅ ማጽደቁን አስታውቋል።
አዋጁ በዋናነት የሚከተሉት ላይ ትኩረት ያደርጋል፡-
ጥራትና ደህንነቱ የተረጋገጠ የተመጣጠነ ምግብ ለሁሉም ዜጎች ተደራሽ ማድረግ፣
በሕፃናትና እናቶች ላይ የሚታየውን የሥርዓተ-ምግብ እጥረት ችግር በሕግ ማዕቀፍ በተደገፈ አሠራር በዘላቂነት መፍታት፣
በምግብ እሴት ሰንሰለት ውስጥ ያሉ ሁሉንም ተዋናዮች በቅንጅት ማሳተፍ።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X