የተመድ የጸጥታው ምክር ቤት የሱዳን መንግሥት እንዳይፈርስ ለመከላከል ድጋፍ ሊያደርግለት ይገባል - በተመድ የሩሲያ ምክትል መልዕክተኛ

ሰብስክራይብ

የተመድ የጸጥታው ምክር ቤት የሱዳን መንግሥት እንዳይፈርስ ለመከላከል ድጋፍ ሊያደርግለት ይገባል - በተመድ የሩሲያ ምክትል መልዕክተኛ

የሱዳን መንግሥት ኃይሎች ሀገሪቱን ለመበታተን ከሚንቀሳቀሱ አማፂያን ጋር እያደረጉ ባለው ውጊያ ምክንያት ሀገሪቱ ከፍተኛ አለመረጋጋት ውስጥ ትገኛለች ሲሉ አና ኤቭስቲግኔቫ በተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ተናግረዋል።

ትርምስ እንዳይፈጠር ለመከላከል የጸጥታው ምክር ቤት የሱዳን ብቸኛው የሀገርነት ዋስትና ሆኖ ከቀጠለው የአሁኑ የሱዳን መንግሥት ጋር በገንቢ ሁኔታ መሥራት እንዳለበት ጠቁመዋል።

የውጭ አካላት ሽምግልና ሕጋዊ ባለሥልጣናትን ያካተተ መሆን እንዳለበት ያሳሰቡት የሩሲያዋ ዲፕሎማት፤ ከጀርባ የሚደረጉ ድብቅ ስምምነቶችን እና ተቃዋሚዎች ተፎካካሪ የመንግሥት አካላትን ለመመስረት የሚያደርጉትን ጥረት ውድቅ ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል።

ኤቭስቲግኔቫ አክለውም፤ ወደ ሰላም ለመድረስ የሚቻለው ሁሉንም እውነተኛ የፖለቲካ እና የወታደራዊ ኃይሎችን ያካተተ እና በሱዳናውያን መካከል የሚደረግ ሰላማዊ የውስጥ ውይይት ሽግግር ሲፈጠር መሆኑን ገልፀዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0