የጋራ ጥቅሞች የሳህል አገራት ጥምረት እና የኢኮዋስ ስብስብን ያገናኛሉ - ኒጀራዊው ባለሙያ
09:04 27.06.2026 (የተሻሻለ: 09:14 27.06.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የጋራ ጥቅሞች የሳህል አገራት ጥምረት እና የኢኮዋስ ስብስብን ያገናኛሉ - ኒጀራዊው ባለሙያ
ከማክሰኞ እስከ ሐሙስ በኡጋዱጉ የተካሄደው ስልታዊ ዐውደ-ጥናት፤ በሳህል ሀገራት ጥምረት እና በኢኮዋስ መካከል ያለውን ግንኙነት የሚመራ ማዕቀፍ ለማዘጋጀት ከቡርኪና ፋሶ፣ ማሊ እና ኒጀር የተወጣጡ ባለሙያዎችን፣ ዲፕሎማቶችን እና ባለሥልጣናትን በአንድ ላይ አሰባስቧል።
የማኅበራዊ-ፖለቲካ እና ኢኮኖሚ ተንታኙ አዳሙ ኡማሩ ለስፑትኒክ አፍሪካ ሲናገሩ፦ “ይህ ጠላቶች ሳንሆን እንዴት አብረን ወደፊት መጓዝ እንደምንችል እንድንመለከት ያስችለናል። ምክንያቱም እኛ በማንኛውም ሁኔታ አብረን ለመቀጠል የቆረጥን ወንድማማቾች ነን” ብለዋል።
እንደ እሳቸው ገለጻ፤ ዋነኞቹ የጋራ ጥቅም ጉዳዮች የሚከተሉት ናቸው፦
▪ ሽብርተኝነትን መዋጋት፤
▪ ጸጥታ እና ደኅንነት፤
▪ የሰዎች እና የሸቀጦች ነፃ ዝውውር።
ኡማሩ አክለውም፤ የሳህል አገራት ጥምረት “ሰላማዊ፣ የተዋሃደ እና የወደፊት ዕጣ ፈንታው በዘላቂነት የተረጋገጠ ቀጠና ለመፍጠር ያለመ ሲሆን፤ ይህም የሁለቱም ስብስቦች ልጆች ለአፍሪካ አህጉር አርአያ እንዲሆኑ ያስችላል” ሲሉ ገልጸዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X