- Sputnik አፍሪካ, 1920
Drum of Changes
ከጥንታዊ የስልጣኔ ምድሮች እስከ ዘመናዊ ከተሞች ልብ፣ በአፍሪካ አዲስ ጥሪ እየተስተጋባ ይገኛል። አፍሪካ የዓለምን የወደፊት ሁኔታ የምትቀርጽ ቸል ልትባል የማይገባት ኃይል ሆና እያደገች ነው። ለአስርት ዓመታት አፍሪካ የምትናገር፣ ነገር ግን የማትደመጥ ሆና ቆይታለች። ዛሬ ግን ጥሪው ግልፅ ነው። አፍሪካ ከዓለም የኃይል ማዕድ የሚገባትን ትክክለኛ ቦታ ትጠይቃለች። ይህ ፕሮግራምም ከአፍሪካ የሚስተጋቡ የለውጥ ድምፆችን በልካቸው ወደ አድማጭ ተመልካቾቹ ያደርሳል።

ከመሠረታዊ ተሟጋችነት እስከ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ማማ፦ የአፍሪካ እውቀት በዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብቶች መዋቅር

ከመሠረታዊ ተሟጋችነት እስከ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ማማ፦ የአፍሪካ እውቀት በዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብቶች መዋቅር
ሰብስክራይብ

“[...] ከስምምነቶች (ኮንቬንሽኖች) ረቂቅ ዝግጅት ጀምሮ እስከ ትግበራቸው ድረስ ያለው አጠቃላይ የሰብአዊ መብቶች ንግግር ግልጽ በሆኑ መዋቅራዊ ምክንያቶች የተነሳ በተወሰኑ እይታዎች [ምዕራባዊ እይታዎች] ብቻ ተፅዕኖ ሲደረግበት ቆይቷል። በዚህም ምክንያት የአፍሪካ ድምፅ እና እይታ ከልዩ የህይወት ተሞክሯችን እና ከአካባቢያዊ እውቀታችን ጋር አብሮ ማምጣት እጅግ አስፈላጊ እና ወሳኝ ነው” የሰብአዊ መብት እና የእኩል ተጠቃሚነት ተሟጋች ኮሚሽነር ርግበ ገብረሓዋሪያ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናገሩ።

የዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን እ.ኤ.አ ሰኔ 9 ቀን 2026 በተ.መ.ድ የአካል ጉዳተኞች መብቶች ኮሚቴ አባል በመሆን የተመረጡትን የኢ.ሰ.መ.ኮ የሴቶች፣ የሕፃናት፣ የአካል ጉዳተኞች እና የአረጋውያን መብቶች ኮሚሽነር ርግበ ገብረሓዋሪያን እንግዳ አድርጓል። ከእርሳቸው ጋር በሚኖረን ቆይታም አፍሪካ የራሷን ተቋማዊ ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ ለምታደርገው ጥረት ምን ትርጉም እንዳለው፣ እንዲሁም የአፍሪካ ሀገርበቀል እውቀትና ልምዶች ዓለም አቀፍ ፖሊሲዎችን እንዴት እየቀረጸ እንደሚገኝ እንመለከታለን።

ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ: Apple PodcastsDeezerSpotifyAfripods Pocket CastsPodcast AddictCastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0