እውቋ የሶቪዬት የጂምናስቲክ ስፖርተኛ የሮማንያን የምልክቶች እገዳ አወገዘች፤ የሩሲያ ቡድን ከውድድሩ ራሱን ማግለሉንም ደገፈች

© telegram sputnik_ethiopiaእውቋ የሶቪዬት የጂምናስቲክ ስፖርተኛ የሮማንያን የምልክቶች እገዳ አወገዘች፤ የሩሲያ ቡድን ከውድድሩ ራሱን ማግለሉንም ደገፈች
እውቋ የሶቪዬት የጂምናስቲክ ስፖርተኛ የሮማንያን የምልክቶች እገዳ አወገዘች፤ የሩሲያ ቡድን ከውድድሩ ራሱን ማግለሉንም ደገፈች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 26.06.2026
ሰብስክራይብ

እውቋ የሶቪዬት የጂምናስቲክ ስፖርተኛ የሮማንያን የምልክቶች እገዳ አወገዘች፤ የሩሲያ ቡድን ከውድድሩ ራሱን ማግለሉንም ደገፈች

የሁለት ጊዜ የኦሊምፒክ የጂምናስቲክ ሻምፒዮን፣ አሰልጣኝ እና ዳኛ ሊዲያ ኢቫኖቫ ለስፑትኒክ እንደተናገረችው፤ የሩሲያ ቡድን የዓለም አቀፉ የጂምናስቲክ ፌዴሬሽንን ይፋዊ ፈቃድ በመጣስ የአካባቢው ከንቲባ የሩሲያን ባንዲራ እና ብሔራዊ መዝሙር በማገዳቸው ምክንያት፤ በሮማንያ ክሉዥ-ናፖካ ከተማ ከሚካሄደው የጂምናስቲክ ውድድር ራሱን ማግለሉ ትክክለኛ ውሳኔ ነው።

“ኤፍአይጂ በመባል የሚታወቀው ዓለም አቀፉ ፌዴሬሽን የሩሲያ ጂምናስቲክ ተወዳዳሪዎች በብሔራዊ መዝሙራቸው እና ባንዲራቸው እንዲወዳደሩ ለመፍቀድ ወስኖ ነበር። ይህም ሩሲያ ለመመለሷን እና እኛን የማይደግፉት እንኳ ሳይቀሩ ይህንን ማመናቸውን የሚያመልከት ይህ ግልጽ ምልክት ነበር” ስትል ገልጻለች።

ድርጊቱን “ትንሽዬ ተንኮሳ” ስትል የጠራችው ኢቫኖቫ፤ ሩሲያ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ለዓለም አቀፉ የስፖርት የግልግል ፍርድ ቤት ይግባኝ በማቅረብ ሕጋዊ እርምጃ እንድትወስድ አሳስባለች።

በማጠቃለያም “ሮማንያ የራሷን ጉዳይ ትመልከት፤ እኛ ደግሞ በምንከበርበት ቦታ ውድድራችንን እናካሂዳለን” ብላለች።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0