ኢትዮጵያ የወደብ ፍላጎቷን ለማሟላት ከተባበሩት የአረብ ኢምሬቶች ጋር የበለጠ ተቀራርባ ልትሠራ ትችላለች - ጌታቸው ረዳ
18:09 26.06.2026 (የተሻሻለ: 18:14 26.06.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ የወደብ ፍላጎቷን ለማሟላት ከተባበሩት የአረብ ኢምሬቶች ጋር የበለጠ ተቀራርባ ልትሠራ ትችላለች - ጌታቸው ረዳ
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትሩ፣ ኢትዮጵያ የወደብና ተያያዥ የመሠረተ ልማት ፍላጎቶቿን ለማሟላት፣ በዘርፉ ሰፊ ልምድና አቅም ካላቸው የተባበሩት የአረብ ኤምሬቶች እና መሰል ሀገራት ጋር ተቀራርባ ልትሠራ እንደሚገባ ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ ወደብ አልባ በመሆኗ ምክንያት ከዓለም አቀፍ የንግድና ደህንነት እንቅስቃሴዎች አንጻር ወሳኝ ፈተናዎች እንደተጋረጡባት ዛሬ መካሄድ በጀመረው የ"ሂሊ ዩኤኢ - አፍሪካ ዲያሎግ" መድረክ ላይ ያነሱት አማካሪ ሚኒስትሩ፤ ችግሩን ለመቅረፍና ዘርፉ የሚጠይቀውን ግዙፍ ኢንቨስትመንት ለመሸፈን ከአጋር ሀገራት ጋር በጋራ መሥራት እጅግ አስፈላጊ ነው ብለዋል።
የተባበሩት የአረብ ኤምሬቶች በአፍሪካ የወደብ ልማት ላይ ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላት የጠቆሙት ጌታቸው ረዳ፤ በአሁኑ ወቅትም ከኢትዮጵያ ጋር በመተባበር በበርበራ ወደብ ልማት፣ በኮሪደር እና በባቡር መሠረተ ልማት ትስስር ላይ በትኩረት እየሠራች እንደምትገኝ አብራርተዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X