ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ በኢትዮጵያ ለ132 ሺህ ዜጎች የግብርና ግብዓቶች ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ

© telegram sputnik_ethiopiaዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ በኢትዮጵያ ለ132 ሺህ ዜጎች የግብርና ግብዓቶች ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ
ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ በኢትዮጵያ ለ132 ሺህ ዜጎች የግብርና ግብዓቶች ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 26.06.2026
ሰብስክራይብ

ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ በኢትዮጵያ ለ132 ሺህ ዜጎች የግብርና ግብዓቶች ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ

ኮሚቴው ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ጋር በመተባበር በአማራ፣ በኦሮሚያ እና በትግራይ ክልሎች ለሚገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎች (22 ሺህ አርሶ አደር አባወራዎችና እማወራዎች) የምርጥ ዘር እና የማዳበሪያ ድጋፍ ማቅረቡን ገልጿል።

‍ ከግንቦት መጀመሪያ እስከ ሰኔ 15 ቀን 2018 ዓ.ም በተከናወነው በዚህ ሰብአዊ መርሃ ግብር፣ በግጭትና በትራንስፖርት እጥረት ሳቢያ እርዳታ ለማድረስ እጅግ አስቸጋሪ በሆኑና በሴቶች ለሚመሩ አቅመ ደካማ ቤተሰቦች ቅድሚያ መሰጠቱ ማኅበሩ ጠቁሟል።

በኢትዮጵያ የዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ኃላፊ ሙላን ጆቫኒኒ ፤ አሁን ላይ የጀመረውና እስከ መስከረም የሚዘልቀው የ“ኤል ኒኞ” የአየር ንብረት መዛባት ዝናብን ሊቀንስ ስለሚችል በምሥራቅ ትግራይና በሰሜን ምስራቅ አማራ የምርት መቀነስ ስጋት እንዳለ ጠቁመው ኮሚቴው ድጋፉን እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0