የኢትዮጵያ የወርቅ ወጪ ንግድ በበጀት ዓመቱ ከ5.5 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ያስገኛል - የማዕድን ሚኒስቴር
15:55 26.06.2026 (የተሻሻለ: 16:04 26.06.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ የወርቅ ወጪ ንግድ በበጀት ዓመቱ ከ5.5 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ያስገኛል - የማዕድን ሚኒስቴር
ይህም ከ2010 ዓ.ም ጋር ሲነጻጸር የ5,000 በመቶ ታሪካዊ ዕድገት ማስመዝገቡን የማዕድን ሚኒስትር ዴኤታ ሃና ብርሃኑ “ኢትዮጵያ ታከናውናለች” በተሰኘው ብሔራዊ ጉባኤ ላይ ገልጸዋል።
መንግሥት እ.ኤ.አ. በ2030 የማዕድን ወጪ ንግድ ገቢን ከ10 ቢሊዮን ዶላር በላይ ለማድረስ እና ኢትዮጵያን ከአፍሪካ አምስት ቀዳሚ የማዕድን አምራች ሀገራት ተርታ ለማሰለፍ አቅዶ እየሠራ እንደሚገኝም ጠቁመዋል።
ባለፉት 30 ዓመታት ያለ ምንም ተጨማሪ እሴት ይላክ የነበረውን የታንታለም ማዕድን በሀገር ውስጥ እሴት ጨምሮ ለገበያ ለማቅረብ መንግሥት ከአንድ የውጭ ኩባንያ ጋር በድርድር ላይ እንደሚገኝም ተመላክቷል።
በተጨማሪም የብረት ምርትን ከውጭ ለማስገባት የሚወጣውን 1 ቢሊዮን ዶላር ለማስቀረት የሚያስችል የስምምነት ውል ተፈርሟል መባሉን ጨምሮ የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።
በሰው ሠራሽ አስተውሎት የበለጸገ ምስል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X