የኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሬ ክምችት 6.8 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል - አፍሪኤግዚም ባንክ

ሰብስክራይብ

የኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሬ ክምችት 6.8 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል - አፍሪኤግዚም ባንክ

የአፍሪካ ኤክስፖርት-ኢምፖርት ባንክ ይፋ ባደረገው የ2026 የአፍሪካ ንግድ ሪፖርት መሠረት፥ የሀገሪቱ የውጭ ምንዛሬ ክምችት ከሁለት ዓመት በፊት እ.ኤ.አ. በ2023 ከነበረበት 2.0 ቢሊዮን ዶላር፣ በ2025 ከሦስት እጥፍ በላይ ዕድገት አስመዝግቧል፡፡

በአመላካችነት የተጠቀሱ ዋና ዋና ማሳያዎች፦

የገቢ ዕቃዎች ሽፋን ፦ የአገሪቱ የውጭ ምንዛሬ ክምችት የገቢ ዕቃዎችን የመሸፈን አቅም ካለፈው ዓመት ከነበረበት የ55 ቀናት ሽፋን አሁን ወደ 3 ወራት ከፍ ብሏል።

የኢኮኖሚ ዕድገት እና የዋጋ ግሽበት፦ ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በ2025 የ9.2 በመቶ የኢኮኖሚ ዕድገት በማስመዝገብ በአፍሪካ ፈጣን ዕድገት ካላቸው አገራት ተርታ ቀዳሚ ሆናለች። በሌላ በኩል ጥብቅ የገንዘብ ፖሊሲን ተከትሎ የዋጋ ግሽበት ከ21.0 በመቶ ወደ 13.2 በመቶ ዝቅ ብሏል።

የአኅጉራዊ ንግድ ዕድገት፦ ኢትዮጵያ ወደ አፍሪካ ገበያ የምትልከው የወጪ ምርት በ26.1 በመቶ በማደግ 2.13 ቢሊዮን ዶላር የደረሰ ሲሆን፥ ከአፍሪካ አገራት የምታስገባው ምርት ደግሞ በ73.4 በመቶ ጭማሪ አሳይቶ 940 ሚሊዮን ዶላር ደርሷል።

ይህ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት አገሪቱ በማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያዎቿ አማካኝነት ወደ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን ሥርዓት ከተሻገረች በኋላ የተመዘገበ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0