የኢትዮጵያ የቡና ማሠልጠኛ ማዕከል ለምስራቅ አፍሪካ የልህቀት ማዕከል ሆኖ እያገለገለ ነው - የኢትዮጵያ ቡና እና ሻይ ባለሥልጣን
17:05 25.06.2026 (የተሻሻለ: 17:14 25.06.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ የቡና ማሠልጠኛ ማዕከል ለምስራቅ አፍሪካ የልህቀት ማዕከል ሆኖ እያገለገለ ነው - የኢትዮጵያ ቡና እና ሻይ ባለሥልጣን
በምስራቅ አፍሪካ ብቸኛው የሆነው ማዕከሉ ብቁ የዘርፉን ባለሙያዎች በማፍራት ረገድ ከአገሪቱ አልፎ ለቀጣናው ሃገራት የልህቀት ማዕከል ሆኖ በማገልገል ላይ እንደሚገኝ የባለሥልጣኑ ዳይሬክተር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሰፊሳ አባቡ ተናግረዋል።
ሰፊሳ አባቡ እንደገለጹት፤ ማዕከሉ በቀጣናው ያለውን የሰለጠነ የሰው ኃይል ክፍተት በመሙላት ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል።
የቡና ጥራት ማረጋገጫ የሚካሄድባቸው 13 ማዕከላት በተለያዩ የሃገሪቱ አካባቢዎች በሥራ ላይ መሆናቸውን ዛሬ በአዲስ አበባ ከተከፈተው 8ኛው የአግሮፉድ ፕላስትፕሪንትፓክ ኢትዮጵያ እና 2ኛው የኢትዮጵያ ቡና እና ምግብ ንግድ ትርዒት ጎን ለጎን መናገራቸውን የስፑትኒክ አፍሪካ ባልደረባ ዘግቧል።
ኢትዮጵያ ባለፈው በጀት ዓመት ከቡና ወጪ ንግድ ከ2.6 ቢሊዮን ዶላር በላይ ማግኘቷን የገለጹት ኃላፊው፤ በመጠናቀቅ ላይ ባለው በጀት ዓመት ይህንን ገቢ ወደ 3 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ እየተሰራ መሆኑን አስታውቀዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X