የዚምባብዌ ሴኔት የፕሬዝዳንቱን የሥልጣን ዘመን ወደ ሰባት ዓመት ለማራዘም የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ አጸደቀ

የዚምባብዌ ሴኔት የፕሬዝዳንቱን የሥልጣን ዘመን ወደ ሰባት ዓመት ለማራዘም የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ አጸደቀ
አሁን ላይ ወደ ትግበራ ለመግባት የፕሬዝዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ ፊርማ የሚጠብቀው ይህ ረቂቅ አዋጅ፤ አስፈላጊውን የሁለት ሦስተኛ ድምፅ ብልጫ በማለፍ በ75 ደጋፊ እና በ4 ተቃውሞ ድምፅ በምክር ቤቱ ፀድቋል።
ዋና ዋና ዝርዝሮች፦
🟠 ረቂቅ ሕጉ ፕሬዝዳንቱ በቀጥታ በሕዝብ ድምፅ ከመመረጥ ይልቅ በፓርላማ እንዲመረጡ የሚያስችል ድንጋጌንም አካትቷል፡፡
🟠 የምናንጋግዋ ሁለተኛው የሥልጣን ዘመን እ.ኤ.አ. በ2028 ያበቃል ተብሎ ይጠበቅ የነበረ ቢሆንም፤ ገዢው የዛኑ-ፒኤፍ ፓርቲ የሀገሪቱን መልሶ የመገንባት አጀንዳ ለማጠናቀቅ ተጨማሪ ጊዜ እንደሚያስፈልጋቸው ተከራክሯል፡፡
🟠 የቀድሞው ምክትል ፕሬዝዳንት እ.ኤ.አ. በ2017 ወታደራዊ ኃይሉ ሀገሪቱን እ.ኤ.አ. ከ1980 ነፃነቷን ካገኘችበት ጊዜ ጀምሮ የገዙትን ሮበርት ሙጋቤን ከሥልጣን ካወረደ በኋላ ነበር ወደ መንበር የመጡት። ምናንጋግዋ ረቂቅ አዋጁን ፈርመው ካጸደቁት እስከ እ.ኤ.አ. 2030 ድረስ በሥልጣን ላይ ለመቆየት ብቁ ይሆናሉ፡፡
🟠 ባለፈው ዓመት የዛኑ-ፒኤፍ ፓርቲ የፕሬዝዳንቱን የሥልጣን ዘመን ለማራዘም ሕገ-መንግሥታዊ ማሻሻያዎችን ለማድረግ ማቀዱን አስታውቆ የነበረ ሲሆን፤ ይህም ባለፈው የካቲት በካቢኔው ድጋፍ አግኝቷል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X