8ኛው የአግሮፉድ ፕላስትፕሪንትፓክ ኢትዮጵያ እና 2ኛው የኢትዮጵያ ቡና እና ምግብ ንግድ ትርዒት መካሄድ ጀመረ

ሰብስክራይብ

8ኛው የአግሮፉድ ፕላስትፕሪንትፓክ ኢትዮጵያ እና 2ኛው የኢትዮጵያ ቡና እና ምግብ ንግድ ትርዒት መካሄድ ጀመረ

ከሰኔ 18 እስከ 20 ቀን 2018 ዓ.ም (ለሦስት ቀናት) የሚቆየው የንግድ ትርዒቱ በአዲስ አበባ ኮንኬንሽን ሴንተር መካሄድ መጀመሩን የስፑትኒክ ባልደረባ ዘግቧል፡፡

ኢትዮጵያ፣ ቻይና፣ ሕንድ፣ ብራዚል፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች እና ግብጽን ጨምሮ ከ18 አገራት የተውጣጡ 153 ታዋቂ ኩባንያዎች ይሳተፉበታል።

መርሃግብሩ በግብርና፣ በምግብና መጠጥ ማቀነባበሪያ፣ በፕላስቲክ፣ በሕትመትና ማሸጊያ ቴክኖሎጂዎች ላይ ያሉ አዳዲስ ፈጠራዎችንና ምርቶችን ማስተዋወቅ ያለመ ነው።

በአሁኑ ወቅት በምስራቅ እና መካከለኛው አፍሪካ ሁለተኛዋ ትልቅ የፕላስቲክ ጥሬ ዕቃ አስመጪ ሀገር የሆነችው ኢትዮጵያ፤ የፕላስቲክ ፍጆታዋ በ1999 ዓ.ም ከነበረበት 44 ሺህ ቶን በ2016 ዓ.ም ወደ 281 ሺህ ቶን ከፍ ማለቱ በመድረኩ ተነስቷል።

ኢትዮጵያ በዚሁ ዘርፍ ለመጠጥና ማሸጊያ ቴክኖሎጂ በዓመት ከ193 ሚሊዮን በላይ ዶላር ወጪ እንደምታደርግም ተገልጿል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0