የኢትዮጵያ የቀድሞዋ ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በተባበሩት መንግሥታት በአዲስ ኃላፊነት ተሾሙ
13:32 25.06.2026 (የተሻሻለ: 13:34 25.06.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ የቀድሞዋ ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በተባበሩት መንግሥታት በአዲስ ኃላፊነት ተሾሙ
የተመድ ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ አንጋፋዋ ዲፕሎማት በምዕራብ አፍሪካና ሳኅል የሚገኘውን የድርጅቱን የፖለቲካ ቢሮ ገለልተኛ ስትራቴጂካዊ ግምገማ እንዲመሩ መመረጣቸውን በይፋ አስታውቀዋል።
ይህ ሹመት የተሰጠው ተቋሙ በቀጣናው ለሚከሰቱ ቀውሶች ፈጣን ምላሽ ከመስጠት አንጻር ያሉበትን የአሠራር ክፍተቶች በጥልቀት ለመመርመርና ውጤታማነቱን ለማሳደግ ታስቦ መሆኑ ተገልጿል።
ሣህለወርቅ በሰኔ ወር መጨረሻ ላይ ሥራቸውን በይፋ የሚጀምሩ ሲሆን፣ መጀመሪያ በኒውዮርክ ከተመድ የፀጥታው ምክር ቤት አባላት ጋር ከተወያዩ በኋላ ቢሮው ወደሚገኝበት ዳካር ሴኔጋል በማምራት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችን እንደሚያነጋግሩ ተጠቁሟል።
ዲፕሎማቷ ቀደም ሲል በሴኔጋል፣ ማሊ፣ ጊኒ እና ኬፕ ቨርዴ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው ያገለገሉ በመሆናቸው፥ የቀጣናው ጂኦ-ፖለቲካዊ ሁኔታና ተግዳሮቶች ጠንቅቀው ማወቃቸው ለዚህ ወሳኝ ኃላፊነት እንዲመረጡ ማድረጉ ተመላክቷል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X