ሩሲያ እና ሞሪታኒያ በሽብርተኝነት እና በሳይበር ስጋቶች ላይ ኃይላቸውን አስተባበሩ - የጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ቢሮ

ሰብስክራይብ

ሩሲያ እና ሞሪታኒያ በሽብርተኝነት እና በሳይበር ስጋቶች ላይ ኃይላቸውን አስተባበሩ - የጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ቢሮ

የሩሲያ ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ አሌክሳንደር ጉትሳን እና የሞሪታኒያ የፍትሕ ሚኒስትር መሐመድ ኡልድ ሱኢዳት አዲስ የትብብር ፕሮቶኮል መፈራረማቸውን የሩሲያ ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ቢሮ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

የሩሲያው ባለሥልጣን በሴንት ፒተርስበርግ ከተካሄደው ስብሰባ በኋላ እንደገለጹት፤ “ድንበር ተሻጋሪ ስጋቶችን ለመከላከል የጋራ የሆኑ ፈተናዎች ከፊታችን ተደቅነዋል። ውጤታማ ምላሽ ለመስጠት ደግሞ ከሕግ አስከባሪ አካላት የተቀናጀ እርምጃ ያስፈልጋል” ብለዋል።

ስምምነቱ የሚከተሉትን ወንጀሎች ለመከላከል የሚደረገውን ትብብር ለማጠናከር ያለመ ነው፦

◻  ሽብርተኝነት እና ፅንፈኝነትን፣

◻  የሳይበር ወንጀልን፣

◻  የዕፅ እና የጦር መሣሪያ ዝውውርን እና 

◻  ሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውርን።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopiaሩሲያ እና ሞሪታኒያ በሽብርተኝነት እና በሳይበር ስጋቶች ላይ ኃይላቸውን አስተባበሩ - የጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ቢሮ
ሩሲያ እና ሞሪታኒያ በሽብርተኝነት እና በሳይበር ስጋቶች ላይ ኃይላቸውን አስተባበሩ - የጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ቢሮ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 25.06.2026
አዳዲስ ዜናዎች
0