አፍሪካ ጥገኝነትን ሳይሆን በራስ መቆምን የሚያበረታቱ ሥርዓተ ትምህርቶች ያስፈልጓታል - ታንዛኒያዊ መምህር
08:00 25.06.2026 (የተሻሻለ: 08:04 25.06.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
አፍሪካ ጥገኝነትን ሳይሆን በራስ መቆምን የሚያበረታቱ ሥርዓተ ትምህርቶች ያስፈልጓታል - ታንዛኒያዊ መምህር
አሁን ያሉ ሥርዓተ ትምህርቶች የጥገኝነት አስተሳሰብን የሚያሰርፁ በመሆናቸው፤ ራሳቸውን የሚችሉ ዜጎች ለማፍራት ማሻሻያ ማድረግ እንደሚገባ አቢሳይ ስቲቨን ንዛሊ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
መምህሩ ያነሷቸው ዐቢይ ነጥቦች፦
ትምህርት፤ ተመራቂዎች ትምህርታቸውን እንዳጠናቀቁ በቀጥታ በራሳቸው ሥራ እንዲሠማሩ የሚያስችላቸውን ተግባራዊ ክህሎት ከማስታጠቅ ይልቅ፤ በተግባር ያልተደገፈና ከመጠን በላይ ፅንሰ-ሀሳብ ላይ የተመሠረተ ሆኗል፣
ራሳቸውን የቻሉ ዜጎች የኢንዱስትሪ ዕድገትን ለማፋጠን፣ ለምርት ዕድገት እና ተጨማሪ መደበኛ ያልሆኑ የሥራ ዕድሎችን ለመፍጠር የሚያስችሉ በመሆናቸው፤ የላቀ የኢኮኖሚ ነፃነት ይፈጥራሉ፣
በአፍሪካ ተጨባጭ እውነታዎች ላይ የተመሠረቱ ሥርዓተ ትምህርቶች፤ የቅጥር አስተሳሰብን በማስቀረት ተመራቂዎች አካባቢያዊ ችግሮችን የሚፈቱና ለማኅበረሰባቸው የሥራ ዕድል የሚፈጥሩ የልማት ሞተሮች እንደሚያደርጋቸው ገልጸዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X