https://amh.sputniknews.africa/20260624/4422706.html
ጋናዊው ጠንቋይ እንግሊዝ ከጋና ጋር አቻ ለተለያየችበት የዓለም ዋንጫ ጨዋታ ተጠያቂ ተደረገ
ጋናዊው ጠንቋይ እንግሊዝ ከጋና ጋር አቻ ለተለያየችበት የዓለም ዋንጫ ጨዋታ ተጠያቂ ተደረገ
Sputnik አፍሪካ
ጋናዊው ጠንቋይ እንግሊዝ ከጋና ጋር አቻ ለተለያየችበት የዓለም ዋንጫ ጨዋታ ተጠያቂ ተደረገ ናና ክዋኩ ቦንሳም ቀደም ብሎ የጋና ብሔራዊ ቡድን እንግሊዝን መቋቋም እንዲችል የእንግሊዝ ቡድን ኮከብ ሃሪ ኬን ላይ ድግምት አድርጌበታለሁ ማለቱን መገናኛ... 24.06.2026, Sputnik አፍሪካ
2026-06-24T18:46+0300
2026-06-24T18:46+0300
2026-06-24T18:54+0300
sputnik africa
telegram sputnik_ethiopia
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/img/07ea/06/18/4422553_55:0:585:298_1920x0_80_0_0_a0cda7f04176ac49e4b9a4489a63450a.jpg
ጋናዊው ጠንቋይ እንግሊዝ ከጋና ጋር አቻ ለተለያየችበት የዓለም ዋንጫ ጨዋታ ተጠያቂ ተደረገ ናና ክዋኩ ቦንሳም ቀደም ብሎ የጋና ብሔራዊ ቡድን እንግሊዝን መቋቋም እንዲችል የእንግሊዝ ቡድን ኮከብ ሃሪ ኬን ላይ ድግምት አድርጌበታለሁ ማለቱን መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል። “ሃሪ ኬን ላይ እየጠመጠምኩበት ነው። ምን ማድረግ እንደምችል ቀደም ሲል አሳይቻለሁ፤ ስለዚህ በሀገሬ ላይ ደምቆ እንዳይታይ ለመከላከል ምን ማድረግ እንዳለብኝ አውቃለሁ። ከባድ ጉዳት እንዲደርስበት አልፈልግም። በጨዋታው እሱን ማክሸፍ ብቻ በቂ ይሆናል። ጋናን ለመርዳት ሥራዬን እሠራለሁ" ሲል ቦንሳም ለአካባቢው መገናኛ ብዙኃን ተናግሮ ነበር ተብሏል። ጋና አቻ መውጣት በቻለችበት በዚህ ጨዋታ፤ ሃሪ ኬን ከጥቂት ርቀት የተገኘውን ግልጽ የግብ ዕድል ሳይጠቀምበት ቀርቷል። እ.አ.አ በ2014 ቦንሳም የፖርቹጋሉ ክሪስቲያኖ ሮናልዶ መጎዳት የእሱ ድግምት ውጤት መሆኑን ገልጾ የነበረ ቢሆንም፤ ተጫዋቹ በማገገሙ ምክንያት ድግምቱ "ሳይሠራ" መቅረቱን ሚዲያዎች አስታውሰዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
Sputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
2026
Sputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
ጋናዊው ጠንቋይ እንግሊዝ ከጋና ጋር አቻ ለተለያየችበት የዓለም ዋንጫ ጨዋታ ተጠያቂ ተደረገ
Sputnik አፍሪካ
ጋናዊው ጠንቋይ እንግሊዝ ከጋና ጋር አቻ ለተለያየችበት የዓለም ዋንጫ ጨዋታ ተጠያቂ ተደረገ
2026-06-24T18:46+0300
true
PT1S
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/img/07ea/06/18/4422553_122:0:519:298_1920x0_80_0_0_d607285ec18375ca3635dada759724a9.jpgSputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
sputnik africa, telegram sputnik_ethiopia
sputnik africa, telegram sputnik_ethiopia
ጋናዊው ጠንቋይ እንግሊዝ ከጋና ጋር አቻ ለተለያየችበት የዓለም ዋንጫ ጨዋታ ተጠያቂ ተደረገ
18:46 24.06.2026 (የተሻሻለ: 18:54 24.06.2026) ጋናዊው ጠንቋይ እንግሊዝ ከጋና ጋር አቻ ለተለያየችበት የዓለም ዋንጫ ጨዋታ ተጠያቂ ተደረገ
ናና ክዋኩ ቦንሳም ቀደም ብሎ የጋና ብሔራዊ ቡድን እንግሊዝን መቋቋም እንዲችል የእንግሊዝ ቡድን ኮከብ ሃሪ ኬን ላይ ድግምት አድርጌበታለሁ ማለቱን መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
“ሃሪ ኬን ላይ እየጠመጠምኩበት ነው። ምን ማድረግ እንደምችል ቀደም ሲል አሳይቻለሁ፤ ስለዚህ በሀገሬ ላይ ደምቆ እንዳይታይ ለመከላከል ምን ማድረግ እንዳለብኝ አውቃለሁ። ከባድ ጉዳት እንዲደርስበት አልፈልግም። በጨዋታው እሱን ማክሸፍ ብቻ በቂ ይሆናል። ጋናን ለመርዳት ሥራዬን እሠራለሁ" ሲል ቦንሳም ለአካባቢው መገናኛ ብዙኃን ተናግሮ ነበር ተብሏል።
ጋና አቻ መውጣት በቻለችበት በዚህ ጨዋታ፤ ሃሪ ኬን ከጥቂት ርቀት የተገኘውን ግልጽ የግብ ዕድል ሳይጠቀምበት ቀርቷል።
እ.አ.አ በ2014 ቦንሳም የፖርቹጋሉ ክሪስቲያኖ ሮናልዶ መጎዳት የእሱ ድግምት ውጤት መሆኑን ገልጾ የነበረ ቢሆንም፤ ተጫዋቹ በማገገሙ ምክንያት ድግምቱ "ሳይሠራ" መቅረቱን ሚዲያዎች አስታውሰዋል።
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X