ኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና ሩዋንዳ በፈቃድ ላይ የተመሠረተ የስደተኞች አመላለስ ሂደትን ለማሻሻል ተስማሙ

ሰብስክራይብ

ኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና ሩዋንዳ በፈቃድ ላይ የተመሠረተ የስደተኞች አመላለስ ሂደትን ለማሻሻል ተስማሙ

​በአዲስ አበባ በተካሄደው የሦስትዮሽ ስብሰባ፤ ሁለቱ ሀገራት ከተመድ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ጋር በመተባበር “በሀገራቱ መካከል የስደተኞችን ደህንነትና ክብር የጠበቀ አመላለስን ለማሳለጥ” ቁርጠኝነታቸውን በድጋሚ ማረጋገጣቸውን ተቋሙ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

ከመግለጫው የተወሰዱ ዋና ዋና ነጥቦች፦

​◻ እ.ኤ.አ ከጥር 2025 ጀምሮ ወደ 8 ሺህ 400 የሚጠጉ ሰዎች ደህንነታቸውና ክብራቸው ተጠብቆ ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።

◻ እ.ኤ.አ በ2026 ደግሞ ተጨማሪ አስር ሺህ ስደተኞች ይመለሳሉ ተብሎ ይጠበቃል።

◻ አስፈላጊውን ሀብት ለማሰባሰብ የለጋሽ ሀገራት እና የልማት አጋሮች ኢንቨስትመንት ወሳኝ ነው።

◻ የስደተኞችን በራስ የመተማመን አቅም ማሳደግ እና በሰብዓዊ እርዳታ ላይ ያላቸውን ጥገኝነት መቀነስ እንደሚያስፈልግ ተገልጿል።

​"የኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የበርካታ አስርት ዓመታት ግጭት እና የአለመረጋጋት አዙሪት፤ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ቤተሰቦችን በተደጋጋሚ ከቄያቸው እንዲፈናቀሉ አስገድዷቸዋል።"

​ በስብሰባው ላይ የተፈረመው የጋራ መግለጫ፤ “የስደተኞች መመለስ ለዘላቂ መፍትሔ፣ ለሰላም ግንባታ እና ለቀጣናዊ መረጋጋት እንደ ምሰሶ” እንደሚቆጠር አፅንዖት ሰጥቷል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0