የናይጄሪያ ፕሬዚዳንት ቦላ ቲኑቡ የአፍሪካ የወሳኝ ማዕድናት ብዝበዛ እንዲያበቃ ጥሪ አቀረቡ
18:07 24.06.2026 (የተሻሻለ: 18:14 24.06.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የናይጄሪያ ፕሬዚዳንት ቦላ ቲኑቡ የአፍሪካ የወሳኝ ማዕድናት ብዝበዛ እንዲያበቃ ጥሪ አቀረቡ
ፕሬዚዳንቱ ጥሪውን ያቀረቡት፤ የማዕድን ሚኒስትሮች ስብስብ የሆነውን የአፍሪካ ማዕድናት ስትራቴጂ ቡድን ልዑካን በቤተ-መንግሥታቸው ተቀብለው ባነጋገሩበት ወቅት ነው።
የቡድኑ የበላይ ጠባቂ ከሆኑት ፕሬዚዳንት ቲኑቡ ንግግር የተወሰዱ ዋና ዋና ነጥቦች፦
▪ "የቀረው ዓለም የእናንተ ሀገር የቆሻሻ ማጠራቀሚያ መሆኑ እንዲሁም ጥሬ ዕቃዎቻችሁን ያለክፍያ መመዝበሩ ግድ አይሰጠውም።"
▪ ማዕድናት በሀገር ውስጥ በሚደረጉ ምርምሮች፣ ልማቶችና ማጣራት አማካኝነት እሴት፣ ቴክኖሎጂ እና ብልጽግናን ማምጣት ይኖርባቸዋል።
▪ ቲኑቡ በአኅጉሪቱ የሚደረጉ የማዕድን ልማት ውይይቶችን ማዕከላዊ ማድረግና በእውቀት ላይ የተመሠረተ ኢኮኖሚ መገንባት እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።
በተጨማሪም፤ የቡድኑ አባላት በዓለም አቀፉ የማዕድን ገበያ ውስጥ የአፍሪካን የመደራደር አቅም እንዲያጠናክሩ አሳስበዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X