ሞሪሸስ በኢትዮጵያ አየር መንገድ አዲስ በረራ ከሩሲያ ጋር የምታደርገውን ግንኙነት ለማሳደግ አቅዳለች

ሰብስክራይብ

ሞሪሸስ በኢትዮጵያ አየር መንገድ አዲስ በረራ ከሩሲያ ጋር የምታደርገውን ግንኙነት ለማሳደግ አቅዳለች

​የአዲስ አበባ-ፖርት ሉዊስ አዲስ በረራ፤ ከሞስኮ እና ከሌሎች የሩሲያ ከተሞች ለሚነሱ ተጓዦች ምቹ የትራንዚት አማራጭ በማቅረብ ለሞሪሸስ ቱሪዝም ዘርፍ መነቃቃት እንደሚፈጥር ተጠብቋል።

 

ሩሲያውያን ተጓዦች ​ከዚህ ቀደም ወደ ሞሪሸስ ለመብረር በዋናነት በኤምሬትስ አየር መንገድ በዱባይ እና በሪያድ ወይም የቱርክ አየር መንገድን በመጠቀም በኢስታንቡል በኩል ይጓዙ እንደነበር የሞሪሸስ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

 

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዲስ በረራ፦

 

ተደራሽነት፣

ጠንካራ የገበያ እምነት፣

ገበያውን በድጋሚ ለማነቃቃት የሚያስችል ጠቃሚ ዕድል እንደሚፈጥር ተነግሯል።

 

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሐምሌ 5 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ሞሪሺስ ዋና ከተማ ፖርት ሉዊስ በሳምንት ሦስቴ በረራዎችን እንደሚጀምር ማስታወቁ ይታወቃል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0