የዩክሬን ጉዳይ አሁንም በፖለቲካዊ እና በዲፕሎማሲያዊ መንገዶች ሊፈታ ይችላል - ላቭሮቭ

ሰብስክራይብ

የዩክሬን ጉዳይ አሁንም በፖለቲካዊ እና በዲፕሎማሲያዊ መንገዶች ሊፈታ ይችላል - ላቭሮቭ

የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በሞስኮ በተካሄደው "የፕሪማኮቭ ንባብ" መድረክ ላይ ያነሷቸው ሌሎች ነጥቦች፦

​▪ ሩሲያ በማንኛውም ጊዜ በዩክሬን ጉዳይ ለመደራደር ዝግጁ ናት፤ ነገር ግን ጠረጴዛው ላይ የሚቀርበው ሐሳብ ከቁምነገር የሚገባ መሆን አለበት።

​▪ ሩሲያ ለዩክሬን ቀውስ ጊዜያዊ መፍትሄዎችን አትቀበልም።

​▪ የአውሮፓ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት አንቶኒዮ ኮስታ ተወካይ ከሞስኮ ተወካዮች ጋር ሁለት ጊዜ ግንኙነት አድርገዋል።

​▪ ፓሪስ ለድርድር ተወካዮቿን ወደ ሞስኮ ልካለች፤ ከለንደን "ልዩ መልዕክተኞችም" ነበሩ።

​▪ ሩሲያ ከዚህ በኋላ በዩክሬን ድርድር ዙሪያ የማንንም ቃል አታምንም።

​▪ የፑቲንን ድጋፍ ያገኘው የአላስካ የአሜሪካ የሰላም ሐሳብ ላይ ሞስኮ እስካሁን ምንም ዓይነት ምላሽ አላገኘችም።

​▪ ትራምፕ ዘለንስኪ በጥልቅ የሩሲያ ግዛቶች ጥቃት እንዲፈጽም ፈቅደዋል የሚሉ የመገናኛ ብዙኃን ዘገባዎች፤ ምኞትን እንደ እውነታ አድርጎ ለማቅረብ የሚደረጉ ሙከራዎች ናቸው።

​▪ የዊትኮፍ እና የኩሽነር የሞስኮ ጉብኝት በውይይት ላይ ነው፤ ሩሲያ ሐሳብቸውን ለመስማት ዝግጁ ናት።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0