የኢትዮጵያ ሜትሮሎጂ ኢንስቲትዩት እና አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የዓለም ሜትሮሎጂ ድርጅት ቀጣናዊ የሥልጠና ማዕከላት ሆነው ተሰየሙ

© telegram sputnik_ethiopiaየኢትዮጵያ ሜትሮሎጂ ኢንስቲትዩት እና አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የዓለም ሜትሮሎጂ ድርጅት ቀጣናዊ የሥልጠና ማዕከላት ሆነው ተሰየሙ
የኢትዮጵያ ሜትሮሎጂ ኢንስቲትዩት እና አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የዓለም ሜትሮሎጂ ድርጅት ቀጣናዊ የሥልጠና ማዕከላት ሆነው ተሰየሙ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 24.06.2026
ሰብስክራይብ

የኢትዮጵያ ሜትሮሎጂ ኢንስቲትዩት እና አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የዓለም ሜትሮሎጂ ድርጅት ቀጣናዊ የሥልጠና ማዕከላት ሆነው ተሰየሙ

 

ስያሜው ኢትዮጵያን የቀጣናው የዕውቀት፣ የክህሎት ልማት እና የፈጠራ ማዕከል እንደሚያደርጋት የኢትዮጵያ ሜትሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታውቋል።

ይህ ውሳኔ የፀደቀው ሰኔ 15 በተካሄደው 80ኛው የዓለም ሜትሮሎጂ ድርጅት ሥራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ነው።

 

ማሠልጠኛዎቹ በሜትሮሎጂ፣ ሃይድሮሎጂ እና የአየር ንብረት አገልግሎቶች ዘርፍ የሥልጠና እና የአቅም ግንባታ የልህቀት ማዕከላት ሆነው እንደሚያገለግሉ ኢንስቲትዩቱ በማኅበራዊ ገጹ ባጋራው መረጃ ገልጿል።

ይፋዊ እውቅናውን ተከትሎም ኢንስቲትዩቱ እና ዩኒቨርሲቲው የሥልጠና አገልግሎቶቻቸውን በሀገር አቀፍ፣ በቀጣናዊ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ማስፋፋትን ጨምሮ ወደ ሙሉ የትግበራ ሥራ እንዲገቡ ይጠበቅባቸዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0