ኢትዮጵያ ዲጂታል ቴክኖሎጂን መሠረታዊ የልማት አጋዥ ኃይል አድርጋ እየተጠቀመችበት ነው - የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር

ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ ዲጂታል ቴክኖሎጂን መሠረታዊ የልማት አጋዥ ኃይል አድርጋ እየተጠቀመችበት ነው - የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር

ሦስተኛው የሳይበር ደህንነት እና የሰው ሠራሽ አስተውህሎት ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል።

በጉባኤው ላይ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ትግስት ሃሚድ፣ ሌሎች የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የአፍሪካ የኢኮኖሚ ኮሚሽን ምክትል ዋና ጸሐፊ ማማ ኬይታ እና ከፍተኛ የሳይበር ደህንነት ባለሙያዎች መገኘታቸውን የስፑትኒክ አፍሪካ ባልደረባ ዘግቧል።

ጉባኤውን በንግግር የከፈቱት ዋና ዳይሬክተሯ፤ ኢትዮጵያ ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት አስተማማኝ እና ስጋቶችን መቋቋም የሚችል የዲጂታል ሥነ-ምህዳር እውን ለማድረግ አመርቂ ተግባራትን አከናውናለች ብለዋል።

"ደህንነቱ የተጠበቀ የዲጂታል ሥነ-ምህዳር የቴክኖሎጂ አስፈላጊ ብቻ አይደለም። ይልቁንም የሀገር ሉዓላዊነት፣ የኢኮኖሚ ጥንካሬ እና የዘላቂ ልማት መሠረታዊ ምሰሶ ነው።"

የኢሲኤ ምክትል ዋና ጸሐፊ በበኩላቸው ኤአይን ለዕድገት ለማዋል በመንግሥት፣ በግል ዘርፍ ተዋናዮች እና በሌሎች ባለድርሻ አካላት መካከል ትብብር ሊኖር እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0