ኪም ጆንግ ኡን አዲስ ደምሳሽ የጦር መርከብ ወደ አገልግሎት አስገቡ
11:35 24.06.2026 (የተሻሻለ: 11:44 24.06.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኪም ጆንግ ኡን አዲስ ደምሳሽ የጦር መርከብ ወደ አገልግሎት አስገቡ
‘ቾይ ሂዮን’ የተሰኘው ባለ 5,000 ቶን ደምሳሽ የጦር መርከብ እያደገ የመጣውን የሀገሪቱን የባሕር ኃይል እና የኒውክሌር አቅም ማሳያ ነው ሲሉ ኪም ጆንግ ኡን በምዕራባዊቷ የወደብ ከተማ ናምፖ በተካሄደው የባሕር ኃይል ሥነ-ሥርዓት ላይ ተናግረዋል።
የመርከቡ ቁልፍ መገለጫዎች፦
የፀረ-አውሮፕላን እና የፀረ-መርከብ ጦር መሣሪያዎች ታጥቋል፣
ኒውክሌር መሸከም የሚችሉ ባሊስቲክ እና ክሩዝ ሚሳኤሎችን ታጥቋል፣
በቅርብ ወራት ውስጥ ከመርከቡ ላይ የተተኮሱ የክሩዝ ሚሳኤሎችን ጨምሮ በተሳካ ሁኔታ ሙከራ ተደርጎበታል።
ኪም በንግግራቸው፤ የሰሜን ኮሪያ የባሕር ኃይል አቅም ከእንግዲህ የባሕር ዳርቻዎቿን በመከላከል ላይ ብቻ የተገደበ አይደለም ማለታቸውን የኮሪያ ማዕከላዊ የዜና ኤጀንሲ ዘግቧል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X