የሩሲያ ባለሙያዎች ሲሸልስ የመጀመሪያውን የዩኔስኮ የባሕል ቅርስ እንድታስመዘግብ ድጋፍ ሊሰጡ እንደሆነ ተዘገበ

ሰብስክራይብ

የሩሲያ ባለሙያዎች ሲሸልስ የመጀመሪያውን የዩኔስኮ የባሕል ቅርስ እንድታስመዘግብ ድጋፍ ሊሰጡ እንደሆነ ተዘገበ

​ከሩሲያ የሳይንስ አካዳሚ የአርኪኦሎጂ ሬስኪው ማዕከል የተወጣጡ አራት ባለሙያዎች፤ በ "ቬንስ ታውን" ፍርስራሽ የ3ዲ ካርታ ሥራ፣ ፎቶግራፍ እና የጂኦስፓሻል ሰነድ ዝግጅት እንደሚያከናውኑ የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

​ባለፈው ሚያዝያ ወር በተፈረመው የሩሲያ-ሲሸልስ የትብብር ስምምነት መሠረት የተዋቀረው ይህ ልዑክ፤ አስቀድሞ የቴክኒክ ግምገማ ያለፈውን የቦታውን የዩኔስኮ ዕጩነት ይደግፋል።​

በዩኔስኮ የዕጩነት ሰነዶች መሠረት ቦታው ታሪካዊ የሆነባቸው ምክንያቶች ፦

▪ ​እ.ኤ.አ በ1876 ከባርነት ነፃ ለወጡ የአፍሪካውያን ልጆች መኖሪያ እና የሙያ ትምህርት ቤት ሆኖ የተመሠረተ ነው፣

▪ ​በሕንድ ውቅያኖስ ቀጣና የባርነት ሥርዓት ማክተም ጋር የተያያዘውን እና ከሲሼልስ ዋነኛ ታሪካዊ ሥፍራዎች የአንዱን ፍርስራሽ ጠብቆ ይዟል፣

▪ ​የሲሸልስ የ "የክሬኦ" ማንነት መፈጠር እና ነፃ ለወጡ የባሪያ ልጆች መደበኛ ትምህርት መጀመርን ያመለክታል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0