አዲሱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የንግድ ፖሊሲ ከአፍሪካ ነጻ የንግድ ትስስር ሕጎች ጋር የተናበበ ነው - የምጣኔ ሀብት መምህር

© telegram sputnik_ethiopiaአዲሱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የንግድ ፖሊሲ ከአፍሪካ ነጻ የንግድ ትስስር ሕጎች ጋር የተናበበ ነው - የምጣኔ ሀብት መምህር
አዲሱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የንግድ ፖሊሲ ከአፍሪካ ነጻ የንግድ ትስስር ሕጎች ጋር የተናበበ ነው - የምጣኔ ሀብት መምህር - Sputnik አፍሪካ, 1920, 24.06.2026
ሰብስክራይብ

አዲሱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የንግድ ፖሊሲ ከአፍሪካ ነጻ የንግድ ትስስር ሕጎች ጋር የተናበበ ነው - የምጣኔ ሀብት መምህር

ሰነዱ ድንበር ተሻጋሪ ንግዶች ከዚህ በፊት ይገጥማቸው የነበሩ የቀረጥ እና ከቀረጥ ወጪ የሆኑ እንቅፋቶችን ለመቅረፍ የሚያስችሉ ድንጋጌዎችን እንዳካተተ የአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ የኢኮኖሚክስ መምህር አሸናፊ ተሾመ ለስፑትኒክ አፍሪካ አብራርተዋል።

"የሕግ ፖሊሲዎቹን፣ የንግድ ስርዓቱን፣ የጉምሩክ አሠራርን፣ ንግዳችንን በጣም ከማዘመን፤ አልፎም ተርፎ የዲፕሎማሲ ሥራዎችን በውስጡ ያካተተ ከመሆኑ አንጻር ከአፍሪካ ቀጣናዊ ንግድ ትስስር ሕጎች ጋር እንዲጣጣም ተደርጎም የተሠራ ነው። ስለዚህ ከዚህ ግዙፍ የንግድ ትስስር ተጠቃሚ ሊያደርጋት የሚችል ወጥ የሆነ ፖሊሲ ነው።"

በተጨማሪም ቴክኖሎጂ፣ ፈጠራ፣ የተማራ ሰው ኃይል እና የምርት ጥራትን ገቢር በማድረግ የንግድ ዘርፉን ለማጎልበት የሚያስችሉ አቅጣጫዎችን እንዳስቀመጠም ባለሙያው አክለዋል።

"ከምንም በላይ የሀገሪቱ የንግድ ሁኔታ ተገማች እንዲሆን ያደርጋል፤ ሕጎች እንዲዋሃዱ ያደርጋል። ይሄ የውጪ ኢንቨስተሮች፣ ትላልቅ ኩባንያዎችን ወደ ሀገር ውስጥ መሳብ ያስችላል።"

በኢትዮጵያ የንግድ ታሪክ የመጀመሪያው የሆነው ሀገራዊ የንግድ ፖሊሲ በቅርቡ በሚኒስትሮች ምክር ቤት መፅደቁ የሚታወስ ነው።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0