የስፑትኒክፕሮ የሰው ሠራሽ አስተውህሎት ሥልጠና የሦስት አኅጉራት ጋዜጠኞችን በሞስኮ አሰባሰበ
19:58 23.06.2026 (የተሻሻለ: 20:04 23.06.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የስፑትኒክፕሮ የሰው ሠራሽ አስተውህሎት ሥልጠና የሦስት አኅጉራት ጋዜጠኞችን በሞስኮ አሰባሰበ
በአካል የሚሰጠው ኤአይ በሚዲያ የተሰኘው የሥልጠና መርኃ-ግብር ከ18 ሀገራት የተወጣጡ 22 ወጣት ጋዜጠኞችን በሞስኮ በማሳተፍ ተጀምሯል።
እስከ ሰኔ 19 ድረስ የሚቆየው ሥልጠና፤ በስፑትኒክ እናት የሚዲያ ግሩፕ ሮሲያ ሴጎድኒያ እና በሩሲያ ሰብዓዊ ኤጀንሲ ሮሶትሩድኒቼስቶቮ የተዘጋጀ ነው።
መርኃ-ግብሩ የአልጎሪዝም ክትትል፣ የድምጽ እና ቪዲዮ ኤዲቲንግን ጨምሮ በሚዲያ የሥራ ሂደት የሰው ሠራሽ አስተውህሎትን እንዴት ተግባራዊ ማድረግ እንደሚቻል በተግባር የተደገፈ ሥልጠና ይሰጣል።
ከዮርዳኖስ፣ ሞሮኮ እና ቬትናም የመጡ ተሳታፊዎች ስሜታቸውን እንደሚከተለው አካፍለዋል፦
ለይት አልአሳፍ፣ አድ-ዱስቱር (ዮርዳኖስ)፦
"የዚህ መርኃ-ግብር ዓለም አቀፋዊ ባህሪ፤ በዓለም ዙሪያ የሚገኙ የሚዲያ ተቋማት የሚጋፈጧቸውን የጋራ ተግዳሮቶች በተመለከተ ውይይት እና ትርጉም ያለው ሃሳብ ለመለዋወጥ ልዩ ምኅዳር ይፈጥራል።"
አጉራም አብደላአዚዝ፣ ሄስፕሬስ (ሞሮኮ)፦
"መርኃ-ግብሩ በሰው ሠራሽ አስተውህሎት ዘመን የጋዜጠኞችን እያደገ የመጣ ፍላጎት በትክክል ያገናዘበ ነው።"
ንጉየን ትዊ ሊን፣ የቬትናም ቴሌቪዥን፦
"የመጀመሪያዎቹ ክፍለ-ጊዜዎች ትኩረቴን በእጅጉ ስበውታል። የሩሲያ ሚዲያ ተቋማት በጋዜጠኝነት ዘርፍ የሰው ሠራሽ አስተውህሎትን እንዴት እያሳደጉት እንደሆነ ማየት በጣም አስደሳች ነው።"
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X