ኒጄር ከዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት ለመውጣት ይፋዊ ጥያቄ አቀረበች
19:53 23.06.2026 (የተሻሻለ: 19:54 23.06.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኒጄር ከዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት ለመውጣት ይፋዊ ጥያቄ አቀረበች
የሀገሪቱ መንግሥት በሰጠው ማብራሪያ፤ "ውሳኔው ፍርድ ቤቱ ሰላምና ፍትሕን በሚሹ ሕዝቦች ዘንድ ትልቅ ተስፋ ጥሎ የነበረ ቢሆንም፤ አሁን ግን አግባብ ላልሆኑ ተግባሮችና ለብዝበዛ መዋል ከመጀመሩ የመነጨ ነው" ብሏል።
በሮም ስምምነት ድንጋጌዎች መሠረት፤ የሀገሪቱ ከፍርድ ቤቱ የመውጣት ውሳኔ የተመድ ዋና ጸሐፊ ማመልከቻውን ከተቀበሉ ከአንድ ዓመት በኋላ ሰኔ 11 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ ተፈጻሚ ይሆናል። ዋና ጸሐፊው የኒጄርን ጥያቄ ሰኔ 11 ቀን መዝግበውታል።
በመስከረም ወር 2018 ዓ.ም ሳኅል ሀገራት ኮንፌዴሬሽን ሥር የተባበሩት ኒጄር፣ ማሊ እና ቡርኪና ፋሶ አይሲሲን "በኢምፔሪያሊዝም እጅ ያለ የኒዮ-ኮሎኒያሊዝም ጭቆና መሣሪያ" ሲሉ በመግለጽ፤ ከፍርድ ቤቱ ለመውጣት ያላቸውን የጋራ ፍላጎት አስታውቀው ነበር።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X