ኢጋድ 7ኛው አጠቃላይ ምርጫ በስኬት በመጠናቀቁ ለኢትዮጵያ መንግሥትና ሕዝብ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፈ

© telegram sputnik_ethiopiaኢጋድ 7ኛው አጠቃላይ ምርጫ በስኬት በመጠናቀቁ ለኢትዮጵያ መንግሥትና ሕዝብ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፈ
ኢጋድ 7ኛው አጠቃላይ ምርጫ በስኬት በመጠናቀቁ ለኢትዮጵያ መንግሥትና ሕዝብ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፈ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 23.06.2026
ሰብስክራይብ

ኢጋድ 7ኛው አጠቃላይ ምርጫ በስኬት በመጠናቀቁ ለኢትዮጵያ መንግሥትና ሕዝብ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፈ

የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ-መንግሥታት ባለሥልጣን፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የምርጫ ሂደቱን በመምራት ረገድ ላሳየው ሙያዊ ብቃትና ቁርጠኝነት አድናቆቱን የገለፀ ሲሆን የምርጫው ሂደት በሰላማዊና በሥርዓት እንዲጠናቀቅ አስተዋጽኦ ላበረከተው ለኢትዮጵያ ሕዝብ ሰላማዊ ተሳትፎም እውቅና ሰጥቷል።

​የምርጫው በስኬት መካሄድ ኢትዮጵያ ለዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታና ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓት ቁርጠኛ እንደሆነች ማሳያ መሆኑን የኢጋድ ሴክሬተሪያት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

አክሎም፤ ሀገሪቱ ብሔራዊ አንድነትን ለማሳደግ፣ አካታች ምክክርን ለማጠናከር እንዲሁም ሰላም፣ መረጋጋትና ቀጣይነት ያለው ልማት ለማስፈን የምታደርገውን ጥረት አጠናክራ እንደምትቀጥል ሙሉ እምነት እንዳለው ገልጿል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0