ኬንያ ለአሜሪካውያን ታካሚዎች ልትገነባ ያቀደችውን የኢቦላ ሕክምና ማዕከል ለጊዜው ማቆሟን የጤና ሚኒስትሩ አስታወቁ
18:51 23.06.2026 (የተሻሻለ: 18:54 23.06.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኬንያ ለአሜሪካውያን ታካሚዎች ልትገነባ ያቀደችውን የኢቦላ ሕክምና ማዕከል ለጊዜው ማቆሟን የጤና ሚኒስትሩ አስታወቁ
በኬንያ ሊገነባ የታቀደው እና በኢቦላ ለተያዙ የአሜሪካ ዜጎች ማቆያነት የሚያገለግለውን ማዕከል በተመለከተ ተጨማሪ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ እስኪሰጥ ድረስ ግንባታው መታገዱን የጤና ሚኒስትሩ አደን ዱአሌ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ገልጸዋል።
ሚኒስትሩ፤ ፍርድ ቤቱ ግንቦት 21 ቀን ማዕከሉ እንዳይገነባ እና አሜሪካውያን ታካሚዎች ወደ ሀገሪቱ እንዳይገቡ የጣለውን ጊዜያዊ እገዳ ወዲያውኑ ባለማክበራቸው ፍርድ ቤቱን ይቅርታ ጠይቀዋል።
በናንዩኪ ከተማ አቅራቢያ በሚገኘው የኬንያ አየር ኃይል የላይኪፒያ አየር ማረፊያ ውስጥ ሊገነባ ታቅዶ የነበረው ይህ ማዕከል፣ በሰኔ ወር መጀመሪያ ከፍተኛ ተቃውሞ ቀስቅሶ እንደነበር ይታወሳል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X