“ኢትዮጵያ መጪውን ጊዜ መድረስ ሳይሆን መኖር ጀምራለች” - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ

ሰብስክራይብ

“ኢትዮጵያ መጪውን ጊዜ መድረስ ሳይሆን መኖር ጀምራለች” - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ

የሀገሪቱ መሪ ይህን ያሉት፤ በኢትዮጵያ መዋቅራዊ የለውጥ እርምጃዎችና ስኬቶች ላይ አተኩሮ “ከለውጥ ወደ ዘላቂ ሽግግር” በሚል መሪ ቃል በተካሄደው ”ኢትዮጵያ ታከናውናለች” በተሰኘው ብሔራዊ ጉባኤ ላይ ነው፡፡

ኢትዮጵያ ባለፉት 8 የለውጥ ዓመታት ለመጪው ትውልድ የሚበጁ ዘመን ተሻጋሪ ሥራዎች መሥራቷን በጉባኤው መክፈቻ ላይ የተናገሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፤ ሀገሪቱ ለቀጣይ ትውልድ ጠንካራ መሠረት ለመጣል በሚያስችሉ የለውጥ እርምጃዎች ውስጥ እንደምትገኝ ጠቁመዋል።

ለውጡ “ከአሁን ይልቅ መጪውን ትውልድ እና ዘመን ታሳቢ ያደረገ ነው” ብለዋል።

በዲጂታል ሥርዓት ግንባታ፣ በግብርና ትራንስፎርሜሽን በማዕድንና በፋይናንስ ዘርፎች መሻሻሎች መኖራቸውንም ተናግረዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0