በሞያሌ አንድ አለቅ የድንበር አገልግሎት ወደ ውጭ ከተላኩ ምርቶች ባለፉት 11 ወራት 56.8 ሚሊዮን ዶላር መሰብሰቡ ተገለጸ

ሰብስክራይብ

በሞያሌ አንድ አለቅ የድንበር አገልግሎት ወደ ውጭ ከተላኩ ምርቶች ባለፉት 11 ወራት 56.8 ሚሊዮን ዶላር መሰብሰቡ ተገለጸ

አገልግሎቱ በኢትዮጵያ እና በኬንያ መካከል ያለውን የንግድ ሥራ ፍሰት ቀልጣፋ እና ውጤታማ ከማድረጉ ባሻገር፤ ለገቢና ወጪ ዕቃዎች አማራጭ የመግቢያና መውጫ በር መሆን እንደቻለ የጉምሩክ ኮሚሽን አስታውቋል።

 

የድንበር ጣቢያው በተጠቀሰው ጊዜ የሰጣቸው አገልግሎቶች፦

የወጪ ንግድ ገቢ፦ ወደ ተለያዩ ሀገራት የግብርና እና የፋብሪካ ምርቶች እንዲላኩ አስችሏል።

የገቢ ንግድ እና ግብር፦ 247 የዕቃ ዓይነቶች ወደ ሀገር ውስጥ የገቡ ሲሆን ከእነዚሁ ምርቶች 5.6 ቢሊዮን ብር ቀረጥና ታክስ ተሰብስቧል።

የኮንትሮባንድ ቁጥጥር፦ ኮንትሮባንድና ሕገ-ወጥ ንግድን ለመከላከል በተደረገው ክትትል 3.6 ቢሊዮን ብር የሚገመቱ የወጪና የገቢ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች በቁጥጥር ሥር ውለዋል።

 

▪ የሞያሌ አንድ አለቅ የድንበር አገልግሎት ህዳር 30 ቀን 2013 ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና በቀድሞው የኬንያ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ተመርቆ ሥራ መጀመሩ የሚታወስ ነው።

 

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0