ሩሲያ የአሜሪካ እና ኢራንን ስምምነት በማወደስ፤ በቀጣይ ውጤታማ ድርድር እንደምትጠብቅ ገለጸች
14:45 23.06.2026 (የተሻሻለ: 14:54 23.06.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ሩሲያ የአሜሪካ እና ኢራንን ስምምነት በማወደስ፤ በቀጣይ ውጤታማ ድርድር እንደምትጠብቅ ገለጸች
"የመካከለኛው ምስራቅ ቀውስ አሁን ላይ ከየትኛውም ጉዳይ በላይ ሆኗል። ሩሲያ የተኩስ አቁሙን እና የአሜሪካ-ኢራን የመግባቢያ ሰነድ ፊርማን በደስታ ትቀበላለች። የተጀመሩት ድርድሮችም ውጤታማ እንደሚሆኑ ተስፋ እናደርጋለን" ሲሉ የክሬምሊን ረዳት ዩሪ ኡሻኮቭ ተናግረዋል።
ረዳቱ ያነሷቸው ሌሎች ቁልፍ ነጥቦች፦
በኤቪያን በተካሄደው የቡድን ሰባት ጉባኤ ላይ የተሳተፉ የምዕራባውያን ሀገራት ጦርነቱን “እስከ መጨረሻው ዩክሬናዊ” ለመግፋት ሲሉ የ “አንኮሬጅ መንፈስን” ለማጥፋት የተቻላቸውን ሁሉ አድርገዋል።
ጉባኤው በቀጠለው “የዩክሬን ድራማ” በምዕራባውያን ሀገራት መካከል ግልጽ የሚና መለዋወጥ የታየበት ነበር።
ሩሲያን ጨምሮ አብዛኛው የዓለም ክፍል በባለብዙ-ዋልታ ምኞቶች እና ምዕራባውያን በጫኑት “በሕግ ላይ የተመሠረተ ሥርዓት” መካከል የተከፋፈለውን ዓለም መቃኘቱን ይቀጥላል።
ክሬምሊን በኢራን ዙሪያ ያቀረበችው የኒውክሌር ጉዳይ ምክረ-ሐሳብ አሁንም እንዳለ ነው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X