ዘለንስኪ በግጭቱ አፈታት ዙሪያ ሞስኮ እና የአውሮፓ ደጋፊዎቿ ላይ ንቀታዊ እና ተግባራዊ የማይሆኑ ቅድመ ሁኔታዎችን እያስቀመጠ ነው - ላቭሮቭ
13:44 23.06.2026 (የተሻሻለ: 13:54 23.06.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ዘለንስኪ በግጭቱ አፈታት ዙሪያ ሞስኮ እና የአውሮፓ ደጋፊዎቿ ላይ ንቀታዊ እና ተግባራዊ የማይሆኑ ቅድመ ሁኔታዎችን እያስቀመጠ ነው - ላቭሮቭ
የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በሞስኮ የዩክሬን ቀውስን የተመለከተ የክብ ጠረጴዛ ውይይት ላይ የሰጧቸው ተጨማሪ መግለጫዎች፦
ዘለንስኪ በቤላሩስ ሥርዓት እንዲመለስ የጠየቀበት ንግግር "ያልተገራ" ነው፣
ሩሲያ የኅብረት መንግሥቱን ለመጠበቅ በስምምነቶች የተቀመጡ እርምጃዎችን በሙሉ ለመውሰድ ዝግጁ ናት፣
ኪየቭ የወታደራዊ ዘመቻዎችን መልክዓ-ምድራዊ ስፋት በመለጠጥ ቤላሩስን ወደ ግጭቱ ለመሳብ እየሞከረች ነው፣
አውሮፓ በዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ውስጥ የሚታየውን የምክንያታዊነት "ጭላንጭል" በማጥፋት፤ በዩክሬን ድርድር ላይ የራሷን ፍላጎቶች በቀጥታ እየጫነች ነው፣
ዘለንስኪ "እውነተኛው ሂትለር ነው፤ ይህ ተሞክሮ ደግሞ ተላላፊ ነው"።
"ምዕራባውያን በዩክሬን ለሂትለር፣ ለናዚ ርዕዮተ ዓለም እና ለምልክቶቹ ያላቸውን ስምምነት ፈጽሞ ያልደበቁት ናዚዎች፣ ሩሲያ ጠሎች እና አምነው የተቀበሉ ፀረ-ሴማውያንን በጥንቃቄ ኮትኩተዋል። እነሱም በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ቀደምቶቻቸው በሩሲያውያን፣ በቤላሩያውያን፣ በአይሁዶች፣ በፖላንዳውያን እና በሌሎች ብሔሮች ላይ በፈጸሙት ወንጀል ይኮራሉ።"
ፈረንሳይ የአፍሪካ መንግሥታትን ለመገልበጥ በምታደርገው ጥረት በዩክሬን ታጣቂዎች ላይ ትተማመናለች።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X