ቶታልኢነርጂስ ከኢትዮጵያ የነዳጅ ገበያ ሊወጣ ነው

© telegram sputnik_ethiopiaቶታልኢነርጂስ ከኢትዮጵያ የነዳጅ ገበያ ሊወጣ ነው
ቶታልኢነርጂስ ከኢትዮጵያ የነዳጅ ገበያ ሊወጣ ነው - Sputnik አፍሪካ, 1920, 23.06.2026
ሰብስክራይብ

ቶታልኢነርጂስ ከኢትዮጵያ የነዳጅ ገበያ ሊወጣ ነው

በኢትዮጵያ ሦስተኛው ትልቅ የነዳጅ አከፋፋይ የሆነው ቶታልኢነርጂስ፤ 120 ገደማ የሚጠጉ ማደያዎቹን ቀደም ሲል "ኦይሊቢያ" በመባል ለሚታወቀውና በመላው አፍሪካ ለሚንቀሳቀሰው ኦላ ኢነርጂ ለመሸጥ ከስምምነት እንደደረሰ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

 

እስካሁን የሽያጭ ገንዘቡ መጠን ይፋ አልተደረገም። ሁለቱ ኩባንያዎች እስካሁን ስለ ስምምነቱ በይፋ የሰጡት ማረጋገጫም የለም።

ግዙፉ የፈረንሳይ ኩባንያ እ.ኤ.አ ከ1950 ጀምሮ በኢትዮጵያ የነዳጅ ችርቻሮ ገበያ ውስጥ የቆየ ሲሆን በነዳጅ ማደያዎቹ እንዲሁም ነዳጅ፣ ፔትሮኬሚካል እና ልዩ ምርቶችን በማቅረብ በሀገሪቱ ታዋቂ መሆን ችሎ ነበር።

 

ቶታልኢነርጂስ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በበርካታ የአፍሪካ ሀገራት ያለውን የነዳጅ ችርቻሮ ንግድ እየቀነሰ ይገኛል። ኩባንያው በተመሳሳይ ማሊን፣ ቡርኪና ፋሶን እንዲሁም ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክን ለቆ ወጥቷል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0