የእስራኤል ወታደሮች በሶማሊላንድ መሠማራታቸው ተዘገበ

© telegram sputnik_ethiopiaየእስራኤል ወታደሮች በሶማሊላንድ መሠማራታቸው ተዘገበ
የእስራኤል ወታደሮች በሶማሊላንድ መሠማራታቸው ተዘገበ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 23.06.2026
ሰብስክራይብ

የእስራኤል ወታደሮች በሶማሊላንድ መሠማራታቸው ተዘገበ

​እስራኤል በታህሳስ ወር ለሶማሊላንድ ነፃነት እውቅና በመስጠት የመጀመሪያዋ ሀገር ከሆነች ጥቂት ጊዜ በኋላ 50 ወታደሮችን ያቀፈ ኃይል ማሠማራቷን ሚዲያዎች አንድ ከፍተኛ የሶማሊያ ባለሥልጣንን ጠቅሰው ዘግበዋል።

የሶማሊያ ፕሬዚዳንት የደህንነት መረጃ አቅራቢ አብዱራህማን ሼክ አዝሃሪ፤ "የእስራኤል ወታደራዊ እና የደህንነት አባላት በሶማሊላንድ መገኘት አዲስ ነገር አይደለም። ከ2025 መጀመሪያ ጀምሮ በርበራ በሚገኘው የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ወታደራዊ ተቋም ውስጥ ሲንቀሳቀሱ መቆየታቸው ነው የሚነገረው" ብለዋል።

​ ተገንጥይዋ የሶማሊያ ክልል ወደ ኢራን ለሚደረጉ የረጅም ርቀት በረራዎች የሚያገለግል ወታደራዊ ጣቢያ ለእስራኤል ሳታመቻች እንዳልቀረ ተዘግቧል። እስራኤል በቀይ ባሕር የባሕር ኃይል ጦር ሠፈር ለመመስረት እንደምትፈልግም ይታመናል።

​"የሶማሊያ መንግሥት አሁን ስለሚቀጥለው እርምጃው በጥንቃቄ ማሰብ አለበት። [...] ይህ እስራኤል ከወደፊት የደህንነት ጥቅሞቿ ጋር በቀጥታ አገናኝታ የምታየው ሰፊ እና የረጅም ጊዜ ስትራቴጂካዊ ፕሮጀክት አካል ነው" ሲሉ አዝሃሪ በኤክስ ገጻቸው ጽፈዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0