https://amh.sputniknews.africa/20260622/4405115.html
የቻይናው ኒውትሬልስ ካፒታል በቀዳሚው የአፍሪካ የኤሌክትሪክ ትራንስፖርት ኩባንያ “ስፓይሮ” 55 ሚሊዮን ዶላር ኢንቨስት አደረገ
የቻይናው ኒውትሬልስ ካፒታል በቀዳሚው የአፍሪካ የኤሌክትሪክ ትራንስፖርት ኩባንያ “ስፓይሮ” 55 ሚሊዮን ዶላር ኢንቨስት አደረገ
Sputnik አፍሪካ
የቻይናው ኒውትሬልስ ካፒታል በቀዳሚው የአፍሪካ የኤሌክትሪክ ትራንስፖርት ኩባንያ “ስፓይሮ” 55 ሚሊዮን ዶላር ኢንቨስት አደረገ ይህም የኩባንያውን አጠቃላይ ኢንቨስትመንት 270 ሚሊዮን ዶላር በማድረስ፤ ስፓይሮን ከ1 ቢሊዮን ዶላር በላይ ዋጋ ላላቸው... 22.06.2026, Sputnik አፍሪካ
2026-06-22T20:15+0300
2026-06-22T20:15+0300
2026-06-22T20:24+0300
sputnik africa
telegram sputnik_ethiopia
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/img/07ea/06/16/4404962_0:67:1280:787_1920x0_80_0_0_7c1f1b9b2f032e0853b4ce5b4c408bfe.jpg
የቻይናው ኒውትሬልስ ካፒታል በቀዳሚው የአፍሪካ የኤሌክትሪክ ትራንስፖርት ኩባንያ “ስፓይሮ” 55 ሚሊዮን ዶላር ኢንቨስት አደረገ ይህም የኩባንያውን አጠቃላይ ኢንቨስትመንት 270 ሚሊዮን ዶላር በማድረስ፤ ስፓይሮን ከ1 ቢሊዮን ዶላር በላይ ዋጋ ላላቸው አዳዲስ ኩባንያዎች ወደሚሰጠው የ "ዩኒኮርን" ደረጃ እንዳቀረበው ኩባንያው ሰኞ ዕለት አስታውቋል።“ስፓይሮ በ ‘ኢነርጂ አብዮት’ የአፍሪካን የትራንስፖርት ዘርፍ እየመራ እንደሆነ እናምናለን። ይህ ሰፊና እጅግ ተስፋ ሰጪ የገበያ ዕድልን ብቻ ሳይሆን፤ ከፍተኛ የንግድ፣ ማኅበራዊ እና አካባቢያዊ እሴት ወደሚፈጥር ትልቅ የመሠረተ ልማት ተቋም የማደግ አቅም እንዳለውም ያሳያል” ሲሉ የኒውትሬልስ ካፒታል አጋር መሥራች ዩፋን ዣንግ ገልጸዋል። ስፓይሮ አሁን ካሉት ሰባት የአፍሪካ ሀገራት ባለፈ 100 ሺህ የኤሌክትሪክ ሞተር ብስክሌቶችን እና 2 ሺህ 500 የባትሪ መለወጫ ጣቢያዎችን ወደ ማላዊ፣ ማሊ እና ኢትዮጵያ ለማስፋፋት ማቀዱን የኩባንያው መስራች ጋጋን ጉፕታ ተናግረዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
Sputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
2026
Sputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/img/07ea/06/16/4404962_72:0:1209:853_1920x0_80_0_0_7d7d1167d52e8a3c51b358ae14fc8ff9.jpgSputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
sputnik africa, telegram sputnik_ethiopia
sputnik africa, telegram sputnik_ethiopia
የቻይናው ኒውትሬልስ ካፒታል በቀዳሚው የአፍሪካ የኤሌክትሪክ ትራንስፖርት ኩባንያ “ስፓይሮ” 55 ሚሊዮን ዶላር ኢንቨስት አደረገ
20:15 22.06.2026 (የተሻሻለ: 20:24 22.06.2026) የቻይናው ኒውትሬልስ ካፒታል በቀዳሚው የአፍሪካ የኤሌክትሪክ ትራንስፖርት ኩባንያ “ስፓይሮ” 55 ሚሊዮን ዶላር ኢንቨስት አደረገ
ይህም የኩባንያውን አጠቃላይ ኢንቨስትመንት 270 ሚሊዮን ዶላር በማድረስ፤ ስፓይሮን ከ1 ቢሊዮን ዶላር በላይ ዋጋ ላላቸው አዳዲስ ኩባንያዎች ወደሚሰጠው የ "ዩኒኮርን" ደረጃ እንዳቀረበው ኩባንያው ሰኞ ዕለት አስታውቋል።
“ስፓይሮ በ ‘ኢነርጂ አብዮት’ የአፍሪካን የትራንስፖርት ዘርፍ እየመራ እንደሆነ እናምናለን። ይህ ሰፊና እጅግ ተስፋ ሰጪ የገበያ ዕድልን ብቻ ሳይሆን፤ ከፍተኛ የንግድ፣ ማኅበራዊ እና አካባቢያዊ እሴት ወደሚፈጥር ትልቅ የመሠረተ ልማት ተቋም የማደግ አቅም እንዳለውም ያሳያል” ሲሉ የኒውትሬልስ ካፒታል አጋር መሥራች ዩፋን ዣንግ ገልጸዋል።
ስፓይሮ አሁን ካሉት ሰባት የአፍሪካ ሀገራት ባለፈ 100 ሺህ የኤሌክትሪክ ሞተር ብስክሌቶችን እና 2 ሺህ 500 የባትሪ መለወጫ ጣቢያዎችን ወደ ማላዊ፣ ማሊ እና ኢትዮጵያ ለማስፋፋት ማቀዱን የኩባንያው መስራች ጋጋን ጉፕታ ተናግረዋል።
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X