የዓለም ባንክ ለጅቡቲ-አዲስ አበባ የንግድ ኮሪደር ማሻሻያ 45 ሚሊዮን ዶላር አጸደቀ

© telegram sputnik_ethiopiaየዓለም ባንክ ለጅቡቲ-አዲስ አበባ የንግድ ኮሪደር ማሻሻያ 45 ሚሊዮን ዶላር አጸደቀ
የዓለም ባንክ ለጅቡቲ-አዲስ አበባ የንግድ ኮሪደር ማሻሻያ 45 ሚሊዮን ዶላር አጸደቀ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 22.06.2026
ሰብስክራይብ

የዓለም ባንክ ለጅቡቲ-አዲስ አበባ የንግድ ኮሪደር ማሻሻያ 45 ሚሊዮን ዶላር አጸደቀ

ይህም ባንኩ ለመንገድ ግንባታው ያደረገውን አጠቃላይ ድጋፍ 205 ሚሊዮን ዶላር ያደርሰዋል።

 

የገንዘብ ድጋፉ ማዕከላዊ ትኩረት የአዲስ አበባ-ጅቡቲ የንግድ ኮሪደር አካል በሆነው የጂቡቲ ብሔራዊ መንገድ 1፤ በአርታ እና በዱዱባላላ መካከል የሚገኙትን ከፍተኛ ተጋላጭነት ያላቸውን ክፍሎች ባለሁለት መጓጓዣ መንገድ አድርጎ ማስፋት ነው።

 

የአየር ንብረት መቋቋም የዚህ ፕሮጀክት ዋና ምሰሶ ሲሆን 70 ኪሎ ሜትር የሚረዝሙ መንገዶች ለአየር ንብረት መቋቋም በሚችሉ ደረጃዎች እንደሚታደሱ ተዘግቧል።

 

የጂቡቲ የኢኮኖሚ እና የፋይናንስ ሚኒስትር ኢሊያስ ሙሳ ዳዋሌህ፤ የጅቡቲ-አዲስ ኮሪደርን ክልላዊ ውህደት፣ ጠንካራ ንግድ እና የጋራ የኢኮኖሚ ዕድገትን የሚደግፍ ስትራቴጂካዊ መንገድ ሲሉ ገልጸውታል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0