በኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የኢቦላ ተጠቂዎች ቁጥር አንድ ሺህ አለፈ

© telegram sputnik_ethiopiaበኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የኢቦላ ተጠቂዎች ቁጥር አንድ ሺህ አለፈ
በኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የኢቦላ ተጠቂዎች ቁጥር አንድ ሺህ አለፈ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 22.06.2026
ሰብስክራይብ

በኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የኢቦላ ተጠቂዎች ቁጥር አንድ ሺህ አለፈ

የዲአርሲ የቅርብ ጊዜ መረጃዎች ምን ያሳያሉ?

​ 1,003 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ 254 ሰዎች ደግሞ ለህልፈት ተዳርገዋል፤ ይህም የሟቾችን መጠን 25.3 በመቶ ያደርሰዋል፤

​ ወረርሽኙ በግንቦት ወር መጀመሪያ ከተቀሰቀሰ ወዲህ 100 ሰዎች ያገገሙ ሲሆን 365 ሰዎች ደግሞ በለይቶ ማቆያ ወይም በሆስፒታሎች ውስጥ የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

የሀገሪቱ የጤና ሚኒስቴር፤ "የበሽታውን ስርጭት ለመግታት የማኅበረሰብ ግንኙነት፣ የምርመራ እና የህክምና ክትትል ሥራዎች ተጠናክረው ቀጥለዋል" ብሏል።

ኡጋንዳ

​ እስከ ያለፈው አርብ ድረስ 19 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ2 ሰዎች ህይወት አልፏል፣

​ 14 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል፣

​ ከግንቦት ወር መጨረሻ ጀምሮ የሞት መጠኑ ምንም ለውጥ አላሳየም።

የበሽታውን ስርጭት ለመግታት የተወሰዱ እርምጃዎች፦

​ የኮንጎ ባለሥልጣናት ከፍተኛ የቫይረሱ ስርጭት በተመዘገበበት የኢቱሪ ግዛት ለሚገኙ ነዋሪዎች የህክምና አገልግሎት ነፃ መሆኑን አስታውቀዋል።

​ በኮንጎ እና በሌሎች ሀገራት የህክምና ቡድኖች፣ የላቦራቶሪዎች፣ የለይቶ ማቆያ ማዕከላት እና የደህንነት መጠበቂያ ቁሳቁሶች ተሰማርተዋል።

​ የመጨረሻ ደረጃ ላይ ለደረሱ ክትባቶች እና ማከሚያዎች የህክምና ሙከራዎች እየተካሄዱ ይገኛሉ።

​ ሩሲያ ከሰባት ሺህ በላይ የኢቦላ ቫይረስ መመርመሪያ የላቦራቶሪ ቁሳቁሶችን ለኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ፣ ለኮንጎ ሪፐብሊክ እና ለኡጋንዳ መላኳ ይታወሳል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0