ደቡብ አፍሪካ ከቻይና ጋር ያላትን የኢኮኖሚ አጋርነት ይበልጥ ለማጠናከር ትሻለች - ምክትል ፕሬዚዳንት ፖል ማሻቲሌ
17:21 22.06.2026 (የተሻሻለ: 17:24 22.06.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ደቡብ አፍሪካ ከቻይና ጋር ያላትን የኢኮኖሚ አጋርነት ይበልጥ ለማጠናከር ትሻለች - ምክትል ፕሬዚዳንት ፖል ማሻቲሌ
ምክትል ፕሬዚዳንቱ በቻይና ዓለም አቀፍ የአቅርቦት ሰንሰለት ኤክስፖ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ "ይህ ዕቅድ ንግድ፣ ኢንቨስትመንት እና የረጅም ጊዜ የኢንዱስትሪ ትብብርን ለማሳደግ ያለመ ነው" ብለዋል።
ፖል ማሻቲሌ ቅድሚያ የሚሰጣቸው የትብብር መስኮችንም ዘርዝረዋል፦
▪ ግብርና እና የምግብ ሥርዓቶች፣
▪ ወሳኝ ማዕድናት እና አረንጓዴ ኢኮኖሚ፣
▪ የላቀ ማኑፋክቸሪንግ፣ ሎጅስቲክ እና የአውቶሞቲቭ ዕሴት ሰንሰለቶች።
በሀገራቱ መካከል ያለው ግንኙነት፤ "እንደ ብሪክስ፣ የቻይና-አፍሪካ ትብብር ፎረም እና በሌሎች ባለብዙ ወገን መድረኮች" አማካኝነት መሻሻሉን ቀጥሏል።
ለጋራ ብልጽግና የተፈረመው የኢኮኖሚ አጋርነት ማዕቀፍ ስምምነት፤ ከቀረጥ ነፃ ዕድል ጋር ተዳምሮ የደቡብ አፍሪካ ምርቶች ወደ ቻይና ገበያ ያለምንም ቀረጥ እንዲገቡ እንደሚያስችልም አክለው ገልጸዋል።
"ሀገራችንን ተመራጭ የኢንቨስትመንት መዳረሻ እና በዓለም አቀፍ የአቅርቦት ሰንሰለት አስተማማኝ የዕሴት ምንጭ ለማድረግ ቁርጠኛ ነን።"
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X