የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት አዳዲስ የንግድ መስመሮችን መክፈቱን አስታወቀ
16:54 22.06.2026 (የተሻሻለ: 17:04 22.06.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት አዳዲስ የንግድ መስመሮችን መክፈቱን አስታወቀ
ድርጅቱ በዚህ ዓመት ወደ ጃፓን፣ ደቡብ ኮሪያ እና ኢንዶኔዥያ አዳዲስ የጉዞ መስመሮችን በመክፈት የንግድ ትስስር እያጠናከረ እንደሚገኝ አስታውቋል።
ይህ አዲስ የንግድ መስመር፦
▪የትራንዚት ጊዜና ወጪ እንደቀነሰ፣
▪የጭነት ማጓጓዣ አቅም እንደጨመረ፣
▪አስመጪና ላኪዎች ፈጣንና ተወዳዳሪ አገልግሎት እንዲገኙ እንዳስቻለ፣
▪የሀገሪቱን የብሉ ኢኮኖሚ ሚና ማጠናከሩን አስታውቋል።
የሀገሪቱን የገቢና ወጪ ንግድ ተወዳዳሪነት ለማሳደግ የተጀመሩ አዳዲስ የመርከብ ስምሪቶች ውጤታማ ሆነው ቀጥለዋል ሲል አገልግሎቱ አክሏል።
🪙 የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ በተቀናጀ የወጪ ቅነሳ ስልቶች በ10 ወራት ከግማሽ ቢሊየን ብር በላይ ወጪ እንዳዳነ ቀደም ሲል አስታውቋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X