የዚምባብዌ ሊቲየም ዘርፍ በዓለም አቀፍ ደረጃ ዋጋ ቢቀንስም 3.4 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንት መሳቡ ተዘገበ

© telegram sputnik_ethiopiaየዚምባብዌ ሊቲየም ዘርፍ በዓለም አቀፍ ደረጃ ዋጋ ቢቀንስም 3
የዚምባብዌ ሊቲየም ዘርፍ በዓለም አቀፍ ደረጃ ዋጋ ቢቀንስም 3 - Sputnik አፍሪካ, 1920, 22.06.2026
ሰብስክራይብ

የዚምባብዌ ሊቲየም ዘርፍ በዓለም አቀፍ ደረጃ ዋጋ ቢቀንስም 3.4 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንት መሳቡ ተዘገበ

የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ፍላጎት መቀነሱን ተከትሎ የሊቲየም ዋጋ እ.ኤ.አ በ2022 ከነበረበት በቶን 86 ሺህ ዶላር በአሁኑ ወቅት ወደ 14 ሺህ 300 ዶላር ገደማ መውረዱን የሀገሪቱ የመንግሥት መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

ይፋዊ መረጃዎች እንደሚያሳዩት የዋጋ መለዋወጥ ቢኖርም፤ የሊቲየም ሽያጭ እ.ኤ.አ በ2026 የመጀመሪያ ሩብ ዓመት 178.64 ሚሊዮን ዶላር ገቢ አስገኝቷል። ይህ ገቢ ባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ከነበረው 84.19 ሚሊዮን ዶላር ጋር ሲነጻጸር የ106 በመቶ ዕድገት አሳይቷል።

የዚምባብዌ አምራቾች ማኅበር ሰብሳቢ ኢንኖሰንት ሩክዌዛ፤ “በእኛ ትንበያ መሠረት እስከ 2030 ድረስ የሊቲየም ኢንዱስትሪው በብሔራዊ ልማት ስትራቴጂ 2 የዕሴት ጭማሪ ፖሊሲ መሠረት፤ በሊቲየም ሰልፌት ላይ ተመስርቶ የ3.2 ቢሊዮን ዶላር ከፍተኛ የሽያጭ መጠን ያስመዘግባል” ብለዋል።

መንግሥት በሀገር ውስጥ ዕሴት መጨመርን ለማበረታታት ካለፈው የካቲት ወር ጀምሮ ያልተጣራ የሊቲየም ክምችት ወደ ውጭ እንዳይላክ ያገደ ሲሆን በመጪው ጥር 2019 ዓ.ም ሙሉ በሙሉ እስኪታገድ ድረስ አዲስ የኮታ አሠራር አስተዋውቋል።

⭕ ሩክዌዛ፤ ዘርፉ በሊቲየም ሰልፌት ፋብሪካዎች፣ በማጣሪያዎች እና በማዕድን ማውጫ ተቋማት አማካኝነት የዕሴት ጭማሪ ለማድረግ ቁርጠኛ እንደሆነ ጨምረው ገልጸዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0