ኢራን በትራምፕ ዛቻ ላይ ተቃውሞ አሰማች፤ በስዊዘርላንድ የሚካሄደው የአሜሪካ እና የኢራን ንግግር ቆመ

ሰብስክራይብ

ኢራን በትራምፕ ዛቻ ላይ ተቃውሞ አሰማች፤ በስዊዘርላንድ የሚካሄደው የአሜሪካ እና የኢራን ንግግር ቆመ

​የኢራን ተደራዳሪ ልዑክ የትራምፕን ዛቻ ተቃውሞ የድርድሩን ቦታ ጥሎ መውጣቱ ተዘግቧል። በተጨማሪም ዛቻው የኃይል አጠቃቀም ወይም ማስፈራሪያ የሚከለክለውን የሰኔ 11ዱን የመግባቢያ ሰነድ የሚጥስ ነው በማለት በይፋ ቅሬታዋን አስገብታለች።

​ቴህራን እስራኤል ከሊባኖስ ካልወጣች እና ጦርነቱ በሁሉም ግንባሮች ካላቆመ በስተቀር ንግግሩ ወደፊት መራመድ አይችልም ስትል ገልጻለች። እስራኤል ወታደራዊ እርምጃዋን ከቀጠለች የከረረ ምላሽ ሊያስከትል እንደሚችል አስጠንቅቃለች። በተጨማሪም ኢራን ዋሽንግተን ንግግሩን ለእስራኤል ጊዜ መግዣነት እየተጠቀመችበት ነው ስትል ከሳለች።

​እንደ አይአርአይቢ ዘገባ፤ ድርድሩ ዳግም ስለመቀጠሉ እስካሁን ግልጽ የሆነ ነገር የለም።

"ዛቻዎቻቸው ሠርተው ቢሆን ኖሮ ዛሬ ካሉበት ተስፋ አስቆራጭ ሁኔታ ውስጥ እንደማይገቡ አይረዱትም? እኛ የአሜሪካውያንን ዛቻ ከቁም ነገር አንቆጥረውም" ሲሉ የኢራን ፓርላማ አፈ ጉባኤ እና በስዊዘርላንድ የድርድር ልዑኩ መሪ የሆኑት መሐመድ ባገር ጋሊባፍ በኤክስ ገጻቸው አስፍረዋል። "እያሰቡ ቢናገሩ ይበጃቸዋል። የጦር ኃይላችን በተለየ መንገድ ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ ነው። እነሱ ማውራታቸውን መቀጠል ይችላሉ፤ እርምጃ የምንወስደው ግን እኛ ነን።"

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0