ብልጽግና ፓርቲ አብላጫ የፓርላማ ወንበር ማሸነፉን ምርጫ ቦርድ አስታወቀ
19:41 21.06.2026 (የተሻሻለ: 19:54 21.06.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ብልጽግና ፓርቲ አብላጫ የፓርላማ ወንበር ማሸነፉን ምርጫ ቦርድ አስታወቀ
ገዥው ፓርቲ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 438 ወንበሮችን በማሸነፍ የአብላጫ ድምፅ ያገኘ ሲሆን ተፎካካሪ ፓርቲዎች እና የግል ተወዳዳሪዎች በአጠቃላይ 48 ወንበሮችን እንዳገኙ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከሰዓታት በፊት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
ምክር ቤቱ በአጠቃላይ 547 ወንበሮች ያሉት ሲሆን ከፍተኛ ወንበር ያሸነፈው ፓርቲ መንግሥት መመሥረት ይጠበቅበታል።
በተጨማሪም ቦርዱ በተመዘገቡ የምርጫ ግድፈቶች ምክንያት በ14 የምርጫ ክልሎች ድጋሚ ምርጫ እንዲካሄድ መወሰኑን ገልጿል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X