ሶማሊያ በታሪክ ከፍተኛ ቁጥር (44 ሺህ) ተማሪዎችን ለ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና አሰቀመጠች - ጠቅላይ ሚኒስትር

ሰብስክራይብ

ሶማሊያ በታሪክ ከፍተኛ ቁጥር (44 ሺህ) ተማሪዎችን ለ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና አሰቀመጠች - ጠቅላይ ሚኒስትር

​የተፈታኞች ቁጥር ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር ከአምስት ሺህ በላይ ጭማሪ ማሳየቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ሐምዛ አብዲ ባሬ በኤክስ ገጻቸው አስታውቀዋል።

ይህ መሻሻል ሊመዘገብ የቻለው በሚከተሉት ምክንያቶች ነው፦

​🟠 በተሻሻለ የደህንነት ሁኔታ፣

🟠 ተጨማሪ የመምህራን ምልመላ፣

🟠 ቀደም ሲል በ "ኸዋሪጅ" አሸባሪ ቡድኖች ቁጥጥር ስር የነበሩ አካባቢዎች ነፃ መውጣታቸው፣

🟠 ቀጣይነት የትምህርት ዘርፍ ማሻሻያዎች።

​“የእያንዳንዱን ሶማሊያዊ ወጣት የስኬታማነት ዕድል ለማረጋገጥ” ፈተናው በመላ ሀገሪቱ በሚገኙ 158 ማዕከላት እንደሚሰጥ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለው ገልጸዋል።

“ይህ አስደናቂ ዕድገት የትምህርት ተደራሽነት መስፋፋትን፣ የሶማሊያ ቤተሰቦችን ጥንካሬ እና አስተዳደራችንን በልጆቻችን መጻኢ ዕድል ላይ መዋዕለ-ንዋይ ለማፍሰስ ቁርጠኛ እንደሆነ ያሳያል።”

​ℹ ሴት ተማሪዎችን ጨምሮ በአጠቃላይ ከ67 ሺህ በላይ ተማሪዎች በዚህ ዓመት በመላ ሶማሊያ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መልቀቂያ ይወስዳሉ።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0